የሐረር ነዋሪዎች በህገወጥ ድርጊቶች መበራከት ስጋት ገብቷቸዋል
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2011ማስታወቂያ
በሐረር ከተማ የቡድን ዝርፊያን ጨምሮ በየቀኑ የሚስተዋሉ ህግ እና ስርዓትን ያልተከተሉ ድርጊቶች መበራከታቸው ህብረተሰቡን በስጋት እንዲኖር አድርጎታል ሲሉ የከተማይቱ ነዋሪዎች ለDW ተናገሩ። ነዋሪዎቹ የኮንደሚንየም ቤታቸው በህገወጦች ተሰብሮ እንተወሰደባቸው እና ከሚኖሩበት ቤት የቀበሌ ቤት በግዴታ እንዲለቅቁ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ ህግ እና ጸጥታን የማስከበር ኃላፊነት ያለባቸው አካላትም ስራቸውን በአግባቡ አለመስራታቸው ችግሩን አባብሶታል ብለዋል። ችግሩ እንዳለ የሚቀበለው የሐረሪ ክልል የፍትህ ቢሮ በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል። የድሬዳዋው ዘጋቢያችን መሳይ ተክሉ ወደ ሐረር ተጉዞ ያጠናቀረውን ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
መሳይ ተክሉ
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ