1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስርዓት አልበኝነትን ለመቅረፍ መተባበር አለብን

ዓርብ፣ ጥቅምት 9 2011

የወቅቱ ትልቅ ፈተና ነው ብለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ያስቀመጡት ስርዓት አልበኝነትን ህዝቡ እና መንግስት ተጋግዘው ይህን ችግር እስካልቀረፉት እንደ ሀገር ለመቀጠል አዳጋች ይሆናል ሲሉ አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/36nOH
Abiy Ahmed Äthiopien
ምስል Reuters/T. Negeri

በመንግሥታቸው ሥራዎችና አንገብጋቢ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል


የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በፕሬዚዳንት የመክፈቻ ንግግር ዙሪያ ዛሬ በምክር ቤቱ ተገኝተው የመንግስታቸውን አቋም ያመላከቱበት ማብራሪያ ብዙ ጉዳዮችን አንስተዋል። የታጠቁ ወታደሮች ወደ ቤተ-መንግስት የመጡበት ሁኔታ ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ብቻ ሳይሆን ፍላጎቱ የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ማጨናገፍ ነበር ማለታቸዉ ሌላዉ ትልቅ የመነጋገርያን ርዕስ ከፍቶአል። ሌላው የወቅቱ ትልቅ ፈተና ነው ብለው ያስቀመጡት ስርዓት አልበኝነት፤ ይህንን ችግር ህዝቡ እና መንግስት ተጋግዘው ካልቀረፉት እንደ ሀገር ለመቀጠል አዳጋች ይሆናል ሲሉ አሳስበዋል። እንድያም ሆኖ መንግስት በሀገሪቱ ግጭቶች እና ስርዓት አልበኝነቶች ሲስተዋሉ ዝብ ብሎ አልተመለከተም  ሲሉ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ተናግረዋል። የዛሬዉን የምክር ቤት ዉሎ በስፍrራዉ ተገኝቶ የተከታተለዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ