ሳዑዲ አረቢያ የሙስና ተጠርጣሪዎችን ለቀቀች
ማክሰኞ፣ ጥር 22 2010ማስታወቂያ
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ባለፈዉ ሕዳር በሙስና ጠርጥሮ ያሰራቸዉን አብዛኞቹን ልዑላን፤ የቀድሞ ባለሥልጣናት እና ቱጃሮችን ለቀቀ።የሐገሪቱ ማስታወቂያ ሚንስቴር ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ተጠርጣሪዎቹ በሙሉ ከነበሩበት ሆቴል ወጥተቃል።በመግለጫዉ መሠረት ከታሰሩት መከካል 381ዱ ሲለቀቁ፤ የተቀሩት 56ት እስረኞች ወደሌላ እስር ቤት ተዛዉረዋል።መንግሥት ከተለቀቁት እስረኞች ከ106 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማስመለሱ ተዘግቧልም።ኢትዮጵያዊዉ ሳዑዲ አረቢያዊዉ ቱጃር ሼኽ መሐመድ ሁሴይን አል አሙዲ ግን ሥለመለቀቅ አለመለቀቃቸዉ ምንም የታወቀ ነገር የለም።
ስለሺ ሽብሩ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ