1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሜርክል ለአራተኛ ጊዜ መራሒተ መንግሥት ሆነዉ ተመረጡ

ረቡዕ፣ መጋቢት 5 2010

ላለፉት 12 ዓመታት በሥልጣን ላይ በመራሒ መንግሥትነት ያገለገሉት አንጌላ ሜርክል ለተጨማሪ አራት ዓመታት መሪ ሆኖ እንዲቀጥሉ በድጋሚ ተመረጡ። ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ከካቢኔ አባሎቻቸዉ ጋር ለሃገር ጥቅም፤ ህዝብ እና ለሃገር ደህንነት እስከ መጨረሻዉ ለመስራት በእግዚአንሄር ስም ቃል እገባለሁ ሲሉ ቃለ መሃላም ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/2uHzL
Deutschland Vereidigung der Bundeskanzlerin
ምስል Reuters/K. Pfaffenbach

በጀርመን ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያላቸው ሦስት ፓርቲዎች አዲስ ጥምር መንግሥት ለመመስረት የደረሱበትን ስምምነት በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ በፊርማ አጽቀዋል።፡፡ፓርቲዎቹ የተፈራረሙት ሥምምነት በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ጀርመንን የሚመራው ጥምር መንግሥት የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች የያዘ ነው።

የስምምነቱን መጽደቅ ተከትሎ የሀገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት አንጌላ ሜርክልን መራሂተ መንግሥት አድርጎ ዛሬ ረቡዕ ይሰየማል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡  ጀርመናውያን ምርጫ ያካሄዱት ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን በምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች መንግሥት መመስረት ባለመቻላቸው መራሂተ መንግሥት ሜርክል ሀገሪቱን በሞግዚትነት ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል፡፡ መንግሥት ሳይመሰረት የተቆየበት የ171 ቀናት ጊዜ በጀርመን ታሪክ ረጅሙ ነው ተብሎለታል፡፡

Deutschland Bundestag Kanzlerwahl
ምስል Getty Images/AFP/O. Andersen

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ