1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማብቂያ የለሹ የደቡብ ሱዳን ቀውስ 

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 30 2010

ግብጽ ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ በአካባቢው የተለየ ሚና በመጫወት ላይ ትገኛለች። የፖለቲካ ተንታኞች ግብጽ ደቡብ ሱዳን ላይ ባልተለመደ መልኩ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ መጀመሯ ኢትዮጵያን ያሰጋል ባይ ናቸው።

https://p.dw.com/p/2xNAU
Südsudan Präsident Salva Kiir und Vizepräsident Riek Machar
ምስል picture-alliance/dpa/P. Dhil

የደቡብ ሱዳን ቀውስ እና የግብጽ ሚና

የእርስ በእርስ ግጭት ለዓመታት ያመሳቀላት የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና ተቃዋሚዎችን የሠላም ስምምነት ንግግር ለማስጀመር የፊታችን ሐሙስ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ቀጠሮ ተይዟል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ ግብጽ ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ በአካባቢው የተለየ ሚና በመጫወት ላይ ትገኛለች። የፖለቲካ ተንታኞች ግብጽ ደቡብ ሱዳን ላይ ባልተለመደ መልኩ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ መጀመሯ ኢትዮጵያን ያሰጋል ባይ ናቸው። የደቡብ ሱዳን ተፋላማዊዎች የሥምምነት ጉባኤ ሁሉንም ወገኖች አስማምቶ የተፈረመው እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር ነሐሴ 15 ቀን 2015 ነበር። ዛሬም ድረስ ግን የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ ሳይኾን፤ የተቀናቃኞቹ ንግግርም ሳይቋጭ እንደተንጓተተ ነው። የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ