1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«መመገቢያ፤መታከሚያም የለንም»ተማሪዎች

ዓርብ፣ ነሐሴ 4 2010

ተለያዩ የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት የሚያስትምሩ ነበሩ።ትምሕርታቸዉን አሻሽለዉ ተመልሰዉ ማስተማር ነዉ-ዕቅዳቸዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከፍላቸዉ ገንዘብ ጊዜዉን ጠብቆ ቢደርሳቸዉ እንኳን ለኑሮ በቂ አይደለም

https://p.dw.com/p/32zJm
Indien Eröffnung der längsten Brücke des Landes in Assam | Modi
ምስል Handout Office Prime Minister of India

Ethiopian Students in India complaints & MoE - MP3-Stereo

ሕንድ ሐገር በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ትምሕርታቸዉን የሚከታተሉ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት የሚከፍላቸዉ የኪስ ገንዘብ በመቋረጡ ወይም በመዘግየቱ ተቸገርን አሉ።ተማሪዎቹ እንደሚሉት ባለፈዉ ሰኔ ማብቂያ ሊከፈላቸዉ የሚገባ ገንዘብ እስካሁን ሥላልተከፈላቸዉ መመገቢያ፤ መታከሚያ እና የመማሪያ ቁሳቁስ መግዢያ አጥተዉ ተቸግረዋል።በሕንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገንዘቡ ከኢትዮጵያ ትምሕርት ሚንስቴር አልደረሰንም ሲል የትምሕርት ሚኒስቴር ግን ገንዘቡ ተልኳል ባይ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።

ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከአንድ ሺሕ ይበልጣሉ።በተለያዩ የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት የሚያስትምሩ ነበሩ።ትምሕርታቸዉን አሻሽለዉ ተመልሰዉ ማስተማር ነዉ-ዕቅዳቸዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት የሚከፍላቸዉ ገንዘብ ጊዜዉን ጠብቆ ቢደርሳቸዉ እንኳን ለኑሮ በቂ አይደለም።አሁን ደግሞ ከቀረ አምስተኛ ሳምንቱን።እሱ አሳም ዩኒቨርስቲ የPHD ተማሪ ነዉ።
                           
የአንድራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ችግር ደግ፤ በዩኒቨርስቲዉ ለPHD የሚያጠናዉ አጥናፉ (ያባቱን ስም አልነገረንም) እንደሚለዉ ከምግብ፤ከፅዳት፤ ከትምሕርት ቁሳቁስ መግዢያ ማጣትም የከበደ ነዉ።ጤና።እሱ የKIIT ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነዉ።የኪስ ገንዘቡ በመዘግየቱ ቤተ-ሰብ ለመጠየቅ ኢትዮጵያ የገቡ ተማሪዎች «ልቆ እና ብድር ለመጠየቅ ተገድዋል።» ይላል
                                           
ኤምባሲ እኛም ደወልን።በኒዉ ደልሒ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የትምህርት ጉዳይ አማካሪ አቶ አሳልፍ ሐብተ ጊዮርጊስ ክፍያዉ መዘግየቱን አልካዱም። የሚደርስበትን ጊዜ ግን መናገር አልፈለጉም።ወይም አያዉቁትም። ትምሕርት ሚኒስቴርም ደወልን።ቃል አቀባይ ሐረጓ ማሞን ጠየቅን።ያለፈዉ በጀት ዓመት ከፍለናል ይላሉ ወይዘሮ ሐረጓ።ቀኑንም ይጠቅሳሉ።
                                        
ዛሬ በኢትዮጵያ ነሐሴ 4፤ በጎርጎሪያኑ 10 ነዉ።የተከፈለዉ ቃል አቀባይዋ እንዳሉት እስከ ሐምሌ አንድ ወይም እስከ ጁን 30 (ሰኔ ማብቂያ) ከሆነ «የሐምሌ ክፍያ የትሔደ?» ይጠይቃሉ ተማሪዎቹ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ