1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለዋልድባ መነኮሳት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ  

ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2010

በፀረ-ሽብር ሕግ በተከሰሱት የዋልድባ መነኮሳት ላይ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ዛሬ የተሰየመዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት አቃቤ ሕግ ምስክር ባለማቅረቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዞአል።

https://p.dw.com/p/2v5da
Symbolbild Deutschland Justiz
ምስል picture-alliance/dpa/U. Deck

«የመነኮሳቱን የአቃቤ ሕግ ምስክርነት ለመታደም በርካታ ሕዝብ ተገኝቶ ነበር»

አቃቤ ሕግ ፖሊስ ምስክሮችን ሊያቀርብ አለመቻሉን እና ያቀረበበትን ምክንያት እንዳልገለፀ በመጥቀስ ያቀረበዉን መከራከርያ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለዉም። በነ አባ ገብረእየሱስ እና አባ ገብረስላሴ ላይ የሚደመጠዉን የአቃቤ ሕግ ምስክርነት ለመታደም በርካታ ሕዝብ ተገኝቶ ነበር። በእለቱ አቃቤ ሕግ የቆጠራቸዉ ምስክሮች እንዳልተገኙ ለዚህም ፖሊስ የሰጠዉ ምክንያት እንደሌለ እና እሳቸዉም እንደማያቁ ለችሎቱ ተናግረዋል። በመሆኑም ለምስክርነት የተቀጠረዉ ለመጀመርያ ጊዜ ስለሆነ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ብለዋል። በቦታዉ ለተገኘዉ የፖሊስ ተወካይ ችሎቱ ለምን ብሎ ጠይቆ ነበር። እሳቸዉም አላዉቅም ሌላ የሥራ ክፍል ነዉ የሚሰራዉ የሚል ምላሽ መስጠታቸዉ ታዉቋል። የተከሳሶች ጠበቆች በበኩላቸዉ ተከሳሶቹ ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ አቃቤ ሕግ በቀጠሮ ሰዓት ምስክሮችን ይዞ መቅረብ እንዳለበት በተደጋጋሚ ማሳሰብያ መሰጠቱን ፤ የምስክርነት ቀጠሮ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ የተሰጠዉ ተብሎ በአቃቤ ሕግ የቀረበ መከራከርያ የሕግም የሥነ ስርዓትም መሰረት የሌለዉ በመሆኑ የሰዉ ምስክር የማሰማት መብቱ ተነፍጎ በሰነድ ማስረጃ ብቻ ብይን ይሰጠን ብለዉ መከራከራቸዉ ታዉቋል። 


ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ