ሀንጋሪ፣ ስሎቫኪያ እና የአውሮጳ ፍርድ ቤት ብይን
ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2009ማስታወቂያ
ፍርድ ቤቱ በዚሁ ትናንት ባሳለፈው ብይኑ ሁለቱ የምሥራቅ አውሮጳ ሀገራት የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን አባል ሀገራት ስደተኞችን በመካከላቸው እንዲከፋፈሉ ባቀረበው ጥያቄ አንጻር ቀደም ሲል የመሰረቱትን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ሰዎች በብዛት ወደ አውሮጳ በፈለሱበት ድርጊት የተፈጠረውን አጣዳፊ ሁኔታ ኮሚሽኑ በማጉላት፣ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ስደተኞችን በማስተናገዱ ረገድ በግሪክ እና በኢጣልያ ላይ ያረፈውን ጫና አባል ሀገራት እንዲጋሩ ለማድረግ የተሰጠ ትክክለኛ ብይን ነው በሚል በደስታ ተቀብሎታል። ሀንጋሪ ግን ብይኑን እንደማትቀበል አስታውቃለች።
ገበያው ንጉሤ
አርይም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ