ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ በይፋ ስልጣን ለቀቁ
ሰኞ፣ መጋቢት 11 2009ማስታወቂያ
በዝግጅቱ ላይ በሃገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በነፃ በጎ አገልግሎት የሚሰጡ 300 ሰዎችን ጨምሮ ባጠቃላይ 600 እንግዶች እንደተገኙ ታዉቋል። ጋዉክ ከዚህ ቀደም በተደረገላቸዉ ቃለ ምልልስ ከእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል።
« ሥልጣኔን ብለቅም የእያንዳንዱ ኅብረተሰብ አካል ሆኜ ከፖለቲከኞች ጎን ይህ የኛ ዴሞክራሴ ነዉ ይህ የኛ ነፃነት ነዉ ብዬ እናገራሉ።»
የ 77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዮአሂም ጋዉክ በእድሜያቸው ምክንያት ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን እንደማይወዳደሩ አሳውቀው ነዉ ስልጣኑን የሚለቁት። ጋውክን የሚተኩት የቀድሞዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ባለፈዉ እሁድ በይፋ ስልጣኑን ተረክበዋል።
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ