1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚዳንት ትራምፕን የሚተቸው መፅሐፍ

ሐሙስ፣ ጥር 3 2010

"Fire and Fury" ሲተረጎም እሳት እና ቁጣ በሚል ርዕስ ስር ታትሞ ሰሞኑን የወጣው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ በብዛት የተሸጠው መፅሐፍ  ዮናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

https://p.dw.com/p/2qhS1
USA Washington Buch "Fire and Fury: Inside the Trump White House"
ምስል Reuters/C. Barria

ምክንያቱም ደራሲው ማይክል ዎልፍ ያወጣው ይህ መፅሐፍ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን የሚተች ነው ። ጸሐፊው የትራምፕን የአመራር ብቃት ብቻ ሳይሆን የአዕምሮ ጤንነታቸውንም ጥያቄ ውስጥ ይከታል። ትራምፕ በበኩላቸው የመፅሀፉ ይዘት ከእውነት የራቀ እንደሆነ በመናገር ያጣጥላሉ።  ስለዚሁ አነጋጋሪ መፅሐፍ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዘገባ አለው።

መክብብ ሸዋ
ልደት አበበ