1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚዳንት ሚሉቲኖቪች በነፃ ተሰናበቱ

ዓርብ፣ የካቲት 20 2001

አምስት ተከሳሾች ከአስራ አምስት እስከ ሀያ ሁለት ዓመታት የሚደርስ የእስራት ቅጣት ተበይኖባቸዋል። ከዋነኞቹ ተዋንያን መካከልም የቀድሞው የዩጎዝላቪያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ኒኮላ ሳይኖቪች አንደኛው ነበሩ ሲሉ ዳኛው አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/H2cY
ሚላን ሚሉቲኖቪች በፍርድ ቤት
ሚላን ሚሉቲኖቪች በፍርድ ቤትምስል ICTY
የቀድሞ ዮጎዝላቪያን የሚመለከተው የተባበሩት መንግስታት ልዩ ፍርድ ቤት ትናንት ውሳኔ አሳለፈ። የሠርቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሚሉቲኖቪች፤ በኮሶቮ በተከሰተው የጦር ወንጀለኝነት ጥፋት ከቀረበባቸው ክስ በነፃ ተሰናብተዋል። ውሳኔውን ይፋ ያደረገውም በኔዘርላንድ ሄግ ያስዋለው ችሎት ነው። ሌሎች አምስት ተከሳሾች ከአስራ አምስት እስከ ሀያ ሁለት ዓመታት የሚደርስ የእስራት ቅጣት እንደተበየነባቸው ታውቓል።