1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፓሪስ፤ ፈረንሳይ የጥቃት ሰለባዎችን አሰበች

ዓርብ፣ ኅዳር 17 2008

በዛሬዉ ዕለት ከሁለት ሳምንት በፊት ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ በደረሰዉ የሽብር ጥቃት ያለፉ እና የተጎዱ ወገኖች በሀገሪቱ በተካሄደ ሥርዓት ታሰቡ።

https://p.dw.com/p/1HDmu
Frankreich Trauer für die Opfer der Anschläge Trauergäste Francois Hollande Orchester
ምስል Getty Images/AFP/P. Wojazer

ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦሎንድ ጥቃቱን የፈፀሙ «የፅንፈኝነት ሠራዊቶች» ያሏቸዉ ላይ አፀፋዉን እንደሚመልሱ ዝተዋል። ለፍርሃትም ሆነ ጥላቻ ቦታ አንሰጥም ያሉት ኦሎንድ፤ ጥቃት አድራሾቹን ፈፅመዉ ለማጥፋትም ለሕዝባቸዉ ቃል ገብተዋል።

«ፈረንሳይ ይህን ወንጀል የፈፀሙትን ፅንፈኞች ለመደምሰስ የሚቻላትን ሁሉ ታደርጋለች። ልጆችዋን ለመከላከልም ካለማቋረጥ ትሰራለች። ፈረንሳይ ሕይወታቸው የጠፋው እንደሚፈልጉትም ሁሉ ራሷን ሆና እንድምቀጥል ቃል እገባላችኋለሁ።»

Frankreich Trauer für die Opfer der Anschläge Trauergäste Invalidendom
ምስል Getty Images/AFP/M. Medina

የዛሬ ሁለት ሳምንት የደረሰዉ እጅግ የከፋ የተባለዉ ጥቃት የ130 ሰዎችን ህይወት ነጥቆ 350ዎቹን ለጉዳት ዳርጓል። ጥቃቱን ያደረሰዉ ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» የሚለዉ ፅንፈኛ ቡድን ነዉ። በመታሰቢያዉ ሥርዓት ላይ ወደ2,600 የተገመቱ ታዳሚዎች መገኘታቸዉ ቢገልፅም ጥቂት የማይባሉ የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች ግን መንግሥት በቂ ርምጃ አልወሰደም በሚል በስፍራዉ እንዳልተገኙ የፈረንሳይ የዜና ወኪል አመልክቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» በሚለዉ ፅንፈኛ ቡድን ላይ በምታካሂደዉ ዘመቻ ሩሲያ ከፈረንሳይ ጋር እንደምትተባበር ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ትናንት አስታዉቀዋል። እንዲያም ሆኖ የሶርያዉን ፕሬዝደንት በሽር አላሳድን ከስልጣን የማስወገዱ ዉሳኔ የሶርያ ሕዝብ መሆኑን ፑቲን አመልክተዋል። ፈረንሳይም በበኩሏ ፅንፈኛዉን ቡድን ለመዋጋት የአሳድ መንግሥትንም ከጎን ማሰለፍ እንደሚገባ ጠቁማለች። የፈንሳይን ሃሳብ የሶርያ መንግሥት መቀበሉን ገልጿል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ