ፍንዳታ በኮንጎ ብራዛቪል
ረቡዕ፣ የካቲት 28 2004ማስታወቂያ
በርካቶች በስሩ ሳይቀበሩ እንዳልቀሩ ስጋት አለ። ቀይ መስቀል ወደስፍራዉ ዘልቆ ለመግባት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ ሲገለፅ አደጋዉ ወደረሰበት ስፍራ የሚወስደዉ መንገድ ጥይት የማይበሳዉ ጃኬት በደረሰቡ ወታደራዊ መኮንኖች መታጠሩም ተገልጿል። ወደሁለት መቶ ሰዎች ህይወት እንደተቀጠፈበት በተነገረዉ በዚህ ፍንዳታ የተጎዱት ከአንድ ሺ ሶስት መቶ እንደሚልቁ፤ ፍንዳታዉ ባስከተለዉ እሳት መዘዝም ወደአምስት ሺ የሚሆኑት ደግሞ ቤታቸዉን ጥለዉ ለመሸሽ መገደዳቸዉ ተዘግቧል። ኮንጎም ለደረሰዉ ጉዳት በብሄራዊ ደረጃ የሃዘን ቀን አድርጋዋለች ዕለቱን።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ተክሌ የኋላ