1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፍርድ ቤት ዳንኤን እና ኤልያስን በነፃ አሰናበተ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 29 2010

በዛሬዉ ዕለት ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን እና የቀድሞዉ አንድነት ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ዳንኤል ሽበሺን በነፃ አሰናበተ። ጉዳዩን የተመለከተዉ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 3ኛ የወንጀል ችሎት በሁለቱም ላይ የቀረበዉን ክስ ዘግቶ ነዉ በነፃ ያሰናበታቸዉ።

https://p.dw.com/p/2nI5p
Addis Ababa - Politiker Daniel Shibeshi und  Journalist Elias Gebru
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ነፃ በመባላቸዉ ቢደሰቱም የደረሰብንን አያካክስም ብለዋል፤

ሁለቱም  ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት በነፃ መሰናበታቸዉ ቢያስደስታቸዉም በክሱ ሰበብ የደረሰብንን እስር እና ድብደባ አያካክስም ብለዋል። ከአዲስ አበባ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ