ፍርድ ቤት የቀረቡት የኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2005የለም አሉ። በሥልጣን ላይ ያለ አንድ የመንግሥት አባል ከተጠቀሰው ፍርድ ቤት ሲቀርብ ፣ ሩቶ የመጀመሪያው ናቸው። በኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ላይ ስለቀረበው ክስና ስለሰውየው ማንነት ተክሌ የኋላ ባጭሩ ያጠናቀረውን ቀጥሎ እናቀርባለን።
የ 46 እና የ 38 ዓመት ጎልማሶች፣ ፖለቲከኛው ዊልያም ሩቶና ጋዜጠኛ ሳንግ ፣
የቀረበባቸው ክስ፤ በታኅሳስ ወር 2000 ዓ ም ፣ በኬንያ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ፣ የያኔዎቹ ተፎካካሪዎች ፤ ምዋይ ኪባኪና ራይላ ኦዲንጋ መካከል ፣ እያንዳንዳቸው አሸናፊ መሆናቸውን የገለጡበት ሁኔታ ማከራከሩን እንደቀጠለ ፤ የጎሣዎች ሁከት ሲቀሰቀስ፤ የወንጀል ተግባራትን በማቀነባበር፤ ግድያ እንዲፈጸም ፣ እንዲሁም ሰዎች ከቀየአቸው እንዲፈናቀሉና እንዲሳደዱ አድርገዋል የሚል ነው።
ያኔ በተወሰደው የኃይል እርምጃ ፤ ቢያንስ 1,200 ሰዎች ሕይታቸውን ሲያጡ፤ 600,000 ቤት- ንብረታቸውን ትተው ፤ ቀየአቸውን ለቀው መሰደድ ግድ ሆኖባቸዋል።
በኪኩዩ ብሔርና በሉዎ ብሔር በተለያዩትም ብሔረሰቦች መካከል ጥላቻ እንዲቀሰቀስ ያደረጉት የፓርቲዎች ተወካዮች መሆናቸው ነው የተመለከተው። የአሁኑ ፕሬዚዳንት ዑሁሩ ኬንያታም፣ በ 2000 ዓ ምህረቱ ምርጫ፤ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪን በመደገፍ ፣ የብሔራቸው አባላት የሆኑትን ኪኩዩዎችን በማነሣሣት ያኔ ለተፈጸመው ግድያና መፈናቀል ኀላፊ ናቸው ተብለው ነው የተከሰሱት ። የእርሳቸው ጉዳይ በደን ኻኹ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤት የሚቀርበው ኅዳር 3 ቀን 2006 ነው።
የካሌንጂን ብሔረሰብ አባል ዊልያም ሩቶ፣ ተሰጥዖ ያላቸው መሪ መሆናቸው በብዙ ኬንያውያን ዘንድ ይነገርላቸዋል። ኬንያዊው የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ ፣ ጆሴፋት ማጉት እንደሚሉት፤ የህይወት ታሪካቸው ፤ ለብዙ ድሆች ኬንያውያን አርአያነት ያለው ነው። ጠንክሮ መማርና መሥራትን በተጨባጭ ሁኔታ ያሳዩ ሰው ናቸውና!
በሰሜናዊው ምዕራብ ኬንያ የተወለዱት ተወልደው ሩቶ፤ በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እያስመዘገቡ ፤ በትርፍ ጊዜያቸውም ምግብ በመሸጥ ፣ ለትምህርታቸው ይከፍሉላቸው የነበሩትን ወላጅ አባታቸውን እየደገፉ ያደጉ ናቸው። እ ጎ አ በ 1990ኛዎቹ ዓመታት መግቢያ ላይ ፤ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አረፕ ሞይ፣ በተጠቀሰው የአገሪቱ ክፍል የሩቶን ት/ቤት ሲጎበኙ ፤ በተካሄደ የትምህርት ቤት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ወጣቱ ተማሪ መሪ ሆነው መቅረባቸውን ትጉኅ ሆነው መታየታቸው አረፕ ሞይን ሳያስደንቅ አልቀረም። ከዚያ በኋላም ነበረ እ ጎ አ በ 1992 በተካሄደው ነጻ ምርጫ ለፓርቲያቸው ወጣቶችን እንዲያደራጁ ሞይ ኀላፊነት የሰጧቸው። አሁን የምክትል ፕሬዚዳንትነት ሥልጣን እስኪደርሱ የኮተኮቷቸው አረፕ ሞይ ናቸው ማለት ይቻላል። በኬንያ የጀርመኑ ፣ የኮንራድ አደናዎር ድርጅት ተጠሪ ካeቴን ዱምል፣ ሩቶ ፤ የሚፈልጉትን የሚያውቁ ሰው ናቸው ይላሉ።
«አቶ ዊልያም ሩቶ፣ የፖለቲካ ስልት በመቀየስ ተሰጥዖ ያላቸው ሰው ናቸው። በመጠየቅና እርዳታ በማግኘትም አያሌ ጉዳዮችን አከናውነዋል። በራሳቸው ጎሳ መካከል ብቻ ሳይሆን ፣ ባጠቃላይ በኬንያ የፖለቲካው ሂደት እንዲሻሻል አስተዋጽዖ ያደረጉም ናቸው። »
ዱምል፣ እንደሚሉት ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት እስከመሆን የደረሱት የ 6 ልጆች አባት ዊልያም ሩቶ፣ ተወዳጅ ናቸው። ጠንክረው በመሥራት ከድህነት ኑሮ ተላቀው እዚህ ደረጃ ለመድረስ በመቻላቸው የሚያደንቁ ጥቂቶች አይደሉም። ተግባራቸው ሁሉ አዎንታዊ ገጽ ብቻ የነበረው ባይሆንም ፣ ኬንያውያኑ ይበልጥ የሚያተኩሩት፤ በጥረታቸውና በደረሱበት ደረጃ ላይ ሆኗል። በሌላ በኩል ደግሞ በክርስትና እምነታቸው ፤ በጰንጠቆስጤ ቤተ ክርስቲያን በትጋት መሳተፋቸው በእምነታቸው ተጋሪዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፎላቸዋል። አሁንም ካርስተን ዱዑመል
«የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ መሆናቸው በአደባባይ እንዲታይላቸው የሚያደርጉ ናቸው፤ሩቶ! በተለይ እ ጎ አ የ 2012 ምርጫ ከተቃረበበት ጊዜ አንስቶ ፣ በየጊዜው ክርስቲያን መሆናቸውን በይፋ ነበረ የሚያሳውቁት።»
የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ደን ኻኽ የቀረቡት ፤ በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም የጦር ወንጀለኞች መርማሪው ፍርድ ቤት አድሎአዊ ነው የሚለው አመለካከት በተስፋፋበት ወቅት ነው። ለምሳሌ ያህል እ ጎ አ በ 2002 የተከሰሱ 18 ግለሰቦች ሁሉም ከአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ብቻ መሆናቸው ተመዝግቦአል። የጦር ወንጀለኞች መርማሪው ፍርድ ቤት ጠ/ዐቃቤ ህግ ፤ ጋምቢያዊቷ ፋቱ ቤንሱዳ ግን ፣ ይህ በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ላይ ወይም በኬንያውያን ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይደለም ፤ ዓላማው ፣ የኅይል እርምጃ ሰለባዎች ለሆኑት ቤሰቦች ፍትኅ ለማስገኘት ነው ብለዋል።
ተክሌ የኋላ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ