ፈተና የገጠመው የሶማልያ የሰላም ጥረት
ሐሙስ፣ ሐምሌ 10 2000ማስታወቂያ
በሀገሪቱ የሽግግር መንግስትና በተቀናቃኞቹ አክራሪዎቹ ሸማቂዎች መካከል በቀጠለው ውዝግብ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሶማልያውያን ተገድለዋል፤ ከሁለት ሚልዮን የሚበልጡም ከመፈናቀላቸው ሌላ፡ በርዳታ አቅርቦት ላይ ጥገኛ ሆነዋል። ይህንኑ ሶማልያን የምትገኝበትን ውዝግብ ለማብቃት የበኩላቸውን ጥረት የጀመሩት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ኑር ሀሰን ሁሴን ከጥቂት ጊዜ በፊት በጅቡቲ የተደረሰው የሰላም ስምምነትን ያልተቀበሉት ተቀናቃኞቹ ወገኖች በድርድሩ እንዲዲሳተፉ ትናንት በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።