ፈረንሣይ፥ በሶሪያ የአየር ድብደባ ጀመረች
እሑድ፣ መስከረም 16 2008ማስታወቂያ
የፈረንሳይ ተባባሪ ብሪታንያ በነሐሴ ወር መጨረሻ ነበር ሶርያ ውስጥ በአማፂው ቡድን ላይ ጥቃት መሰንዘር የጀመረችው። ብሪታንያና ፈረንሣይ የአይ ኤስ ቡድንን ለመዋጋት ዩናይትድ ስቴትስ ኢራቅ ውስጥ በምታኪያሂደው ትግል ቢጣመሩም ሶርያ ውስጥ በሚኪያሄደው የእርስ በዕርስ ጦርነት ግን ጣልቃ መግባቱን ሸሽተው ቆይተው ነበር።
በሌላ በኩል ሩስያ፣ ሶርያ፣ ኢራቅና ኢራን አሸባሪው የአማፂ ቡድንን በጋር ለመውጋት ትብብር መጀመራቸውን ይፋ አደረጉ። የኢራቅ ጦር እንደገለፀው አራቱ እገራት መረጃ የሚለዋወጡበት አንድ የጋራ ማዕከል መስርተዋል። ይህ አዲስ የትብብር ሥራ ሩስያ በአካባቢው ያላትን ሚና ከፍ ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል። ምዕራባውያን በተደጋጋሚ ሩስያ የሶርያው መሪ የበሽር አል አሳድን ጦር ትደግፋለች በሚል ሲወቅሷት ሰንብተዋል።
ልደት አበበ
ማንተጋፍቶት ስለሺ