1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፀረ ጆሴፍ ኮኒ ዘመቻ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 16 2004

እራሱን የጌታ ተፋላሚ ብሎ የሚጠራው በእንግሊዘኛ ምህጻሩ LRA የተባለው የዮጋንዳ አማፂ ቡድን መሪ -ጆሴፍ ኮኒንን አጥብቀው የሚሟገቱ ወገኖች የኮኒን ፎቶ በየከተሞቻቸው ዛሬ ማታ በመለጠፍ በነገው ዕለት የጆሴፍ ኮኒን ማንነት ለሕህዝቦቻቸው ለማሳወቅ ተነስተዋል።

https://p.dw.com/p/14hf5
Screenshot Youtube Slogan Cover the night
ምስል Youtube

እራሱን የጌታ ተፋላሚ  በእንግሊዘኛው LRA ብሎ የሚጠራው የዮጋንዳ አማፂ ቡድን መሪ -ጆሴፍ ኮኒንን በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ፊት ለማቅረብ የተደረጉ በርካታ ሙከራዎች እስካሁን ከሽፎዋል። በዚህም የተነሳ የአለም አቀፉ ህዝብ በኮኒ ላይ እንዲዘምት INVISIBIL CHILDREN የተሰኘው ድርጅት በቅርቡ አንድ ቪዲዮ በYOU TUBE ማውጣቱ ይታወሳል። በእርግጥ ነገ ከእንቅልፋችን ስንነሳ በየምንኖርበት ከተማ «የጌታ ተፋላሚ» ብሎ እራሱን የሚጠራው ቡድን  LRA መሪ -ጆሴፍ ኮኒን ምስል በየቦታው ተለጥፎ እንመለከት ይሆን? የነገ ሰው ይበለን! ሕፃናትን በኃይል እያስገደደ ለውጊያ በመመልመሉ የሚታወቀው እና በተለይ ቡድኑ ይንቀሳቀስበት በነበረው የሰሜን ዩጋንዳ አካባቢ ሕዝብ ላይ ዘግናኝ የጭካኔ ተግባር ቡድኑ ፈፅመዋል። ኮኒን በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ፊት ለማቅረብ የተደረጉ በርካታ ሙከራዎች እስካሁን አልተሳካም።  ኮኒ በምስራቅ አፍሪቃ እንደሚኖር ይገመታል። ቡድኑም በአሁኑ ሰዓት ተዳክሟል። ይሁን እና INVISIBIL CHILDREN የተሰኘው ድርጅት የአለም አቀፉን ህዝብ በኮኒ ላይ ለማዝመት ተነስቷል።  ሀሳቡን በርካታ ዮጋንዳውያን ይተቹታል።

«በግሌ የማስበው ይህ  ዘመቻ ዘግይቷል ብዬ ነው። ይህ ቪዲዮ ከ10 አመት በፊት ነበር መውጣት የነበረበት። ቪዲዮው እስከወጣ ጥረስ ማንም ስለ ኮኒ አያወራም ነበር። »ይላል። ዮጋንዳዊው ኢቫን አትዊነ ። ጆሴፍ ኮኒ እና የINVISIBIL CHILDREN ቪዲዮ በአሁኑ ሰዓት በመዲናይቱ ካምፓላ የመወያያ ርዕስ ነው።

Screenshot Joseph Kony 2012 Youtube-Video http://www.youtube.com/watch?v=Y4MnpzG5Sqc Bild: 09.03.2012 ***Bild nur im Zusammenhang mit der Berichterstattung über das betreffende Youtube-Video zu verwenden***
ጆሴፍ ኮኒምስል youtube.com

«አንዳንድ ሰዎች ቪዲዮው ጥሩ ነው ይላሉ። ጥሩ ነው የሚሉበት ምክንያት ማንኛውም ማስታወቂያ ለአንድ አገር ጥሩ ነው በሚል ነው። ይበልጡ ህዝብ ግን ቪዲዮውን አልተቀበለውም። ጥሩ ያልሆነ ማስታወቂያ ነው፤ ነው የሚለው። በአሁኑ ሰዓት እዚያ እንደሌለ አይናገሩም። »INVISIBIL CHILDREN በርካታ ትችት ቀርቦበታል። የፖለቲካ ተንታኞች እና ዮጋንዳዊያን ፊልሙ፤ የጭካኔውን ተግባር በበቂ ሁኔታ የሚያሳይ ሳይሆን ማስታወቂያ ነው ይላሉ። «KONY 2012 » የተሰኘው ቪዲዮ ሁለት ወር በማይሞላ ጊዜ 88 ሚሊዮን ጊዜ በYOU TUBE ተጎብኝቷል። ታዋቂ አቀንቃኞች እንደ ሌዲ ጋጋ፣ ሪኻና እና አንጀሊና ጆሊ የመሳሰሉ ተዋንያን ዘመቻውን ይደግፋሉ። ጋዜጠኛ አሊስ ኪንጊ ግን ለምን አሁን ትላለች?

« ኮኒ ከዮጋንዳ ከወጣ ከ5 እስከ 7 ዓመታት ተቆጥረዋል።  እኔን በግሌ የሚረብሸኝ ነገር ምንድን ነው፦ ለምንድን ነው ሰሜን ዮጋንዳ ሰላም በሰፈነበት ሰዓት እንዘዚህ አይነት ቪዲዮ በኢንተርኔት እየተሰራጨ ያለው? ወሳኝ በነበረበት ወቅት ለምን አልወጣም? በግሌ የምለው ይህ ገንዘብ ማግኛ ብቻ ነው። አስታውሺ፤ ዮጋንዳ ቅርብ ጊዜ ግዙፍ የነዳጅ ዘይት ያገኘት ታዳጊ አገር ነች።  እኔ ይህንን የኮኒ ቪድዮ ከጥቅም ጋ የተገናኘ ነው ባይ ነኝ። »

ድርጅቱ የርዳታውን ገንዘብ ያለአግባብ ያጠፋል የሚሉ ትችቶች በአንዳንድ የኮኒ ቪዲዮ በተለጠፉባቸው ድረ ገፆች ላይ ይነበባሉ። የዛኑም ያህል የተፈፀመው ድርጊት ያሳዘናቸው እና ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ኮኒ የሰሙ ወጣቶች የሰጡት አስተያየት ይነበባል።   በአውሮፓ የምትኖረው  ጋዜጠኛ አሊስ ኪንጊ ዛሬ ማምሻውን ስለታቀደው የማስታወቂያ ልጠፋ ምን ትላለች?

Kristen Bell & Jason Russell pose with participants at The Invisible Children's "THE RESCUE" Rally at City Hall in Santa Monica, California on April 25,2009 Copyright 2009 Debbie VanStory/ iPhoto Photo via Newscom Picture-Alliance
ጆሴፍ ኮኒ የሚሞግቱ ወገኖችምስል picture-alliance/Newscom

«ኮኒ ዮጋንዳ ውስጥ የለም።  ዘመቻው እና በአለም አቀፍ በሙሉ የፎቶ ልጠፋው በሙሉ የማይጠቅም ነው።  እኚህ በድረ ገፆች ላይ አስተያየት የሚሰጡት ዮጋንዳን ጎብኝተው የማያውቁ ዮሮፓውያን፣ አምባ ገነን ፕሬዘደንት ነው ያላችሁ የሚሉት በሙሉ ትርጉም የለሽ ነው። ኮኒ ዮጋንዳ የለም። ሰላም ነው ያለው። ስለዚህ በአለም አቀፍ ዘንድ የኮኒን ፎቶ መለጠፉ ለምኑ ነው? »

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ