ጥንቃቄ ለአይናችን
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2005ማስታወቂያ
በሀገሪቱ የዓይን ማዝ በሁለተኛ ደረጃ የሰዎችን የአይን ብርሃን አሳጥቶ ለአይነስዉርነት የሚዳርግ መሆኑም ተደርሶበታል። ORBIS ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በሚሰጠዉ የዓይን ጤና አገልግሎት 132 ሺህ አዋቂዎችና ህፃት ምርመራ እንደተደረገላቸዉ፤ 480 ሺህ ያህሉ ደግሞ ህክምና እንዳገኙ በድረገፁ ላይ ያሰፈረዉ መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ስራ ከጀመር ከአስር ዓመት በላይ የሆነዉ ኦርቢስ ኢንተርናሽናል፤ በዚህ ጊዜ ዉስጥ ታዲያ አሳሳቢዉን የአይነስዉርነት መንስኤ አይነማዝን፤ የአይን ሞራ እና ሌሎች ችግሮችን ኅብረተሰቡ ዉስጥ ገብቶ ከማከም በተጨማሪም ለአይን ሃኪሞች የሙያ ማበልፀጊያ ስልጠናዎችን እያስፋፋ እንደሚገኝ የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶክተር አለማየሁ ሲሳይ ይናገራሉ።
ሰዎች ለግል ንፅህና ቅድሚያ በመስጠት እጅና ፊታቸዉን አዘዉትረዉ መታጠብን እንዳይዘነጉ፤ አካባቢያቸዉንም ማፅዳቱ የአይን ማዝ በሽታን ለምታስተላለፈዉ ዝንብ እድሉን እንደሚነሳት ነዉ ያመለከቱት። አይነማዝ እንዲሁም የአይን ሞራ በርካቶችን ለአይነስዉርነት ሲዳርጉ እነዚህ የዓይን ጤና ችግሮችን በቀላሉ ማከም እንደሚቻል፤ ማየት የተሳናቸዉ ወገኖችም ብርሃን ዳግም የሚያገኙበት ሁኔታ ኢትዮጵያም ዉስጥ ተመቻችቷል።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋድ መሐመድ