1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥቃት በአፍጋኒስታንና ጀርመን

ሐሙስ፣ ነሐሴ 10 1999

ትናንት በአፍጋኒስታን በተጣለ ጥቃት ሶስት የጀርመን ፖሊሶች ተገደሉ፡

https://p.dw.com/p/E87o
መራሂተመንግስት ሜርክል ሀዘናቸውን ሲገልጹ
መራሂተመንግስት ሜርክል ሀዘናቸውን ሲገልጹምስል AP
አንድ ሌላ ደግሞ ቆሰለ። በሁለት ተሽከርካሪዎች ይጓዙ በነበሩት ራሳቸውን ለመከላከል እንኳን ዕድል ያላጋጠማቸው እና የተኩስ ስልጠና ለማካሄድ ይጓዙ የነበሩት ጀርመናውያን ፖሊሶች ላይ የተጣለውን ጥቃት ያየ አንድ አፍጋናዊ ገበሬ ሁኔታውን እንዲህ ነበር የገለጸው። « ብዙ መኪኖች ነበሩ፤ ሁለተኛው ተሽከርካሪ በፍንዳታው ተጎዳ፤ ከአስር ደቂቃ በኋላም ሄሊኮፕተሮች መጥቶ በርካታ ሰዎችን ወስደዋል። »
ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ ይገኝ በነበረውና ብዙም ባልተጎዳው ተሽከርካሪ የነበሩት ተሳፋሪዎች ወዲያውኑ የተጎዱትን የማዳን፡ እንዲሁም የሞቱትን የማንሳት ርምጃ መውሰዳቸውንም ገበሬው አክሎ ገልጾዋል። በጀርመን መንግስት ዘገባ መሰረት፡ በጥቃቱ የሞቱት ጀርመናውያን በአፍጋኒስታን በሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ አንጋቾች ኃላፊ፡ አንድ የፌዴራዊው ወንጀለኛ ጉዳይ ተመልካች መስሪያ ቤት ኮሚሽነርና አንድ ሶስተኛ አንጋች ነበሩ። የጀርመን ፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን ኔቶ በሚመራውና በምህጻሩ አይዛፍ እየተባለ በሚታወቀው በይበልጥ የመልሶ ግንባታ ስራ የሚያከናውኑትን እና መረጋጋታ ያለባቸውን አካባቢዎችን የመጠበቅ ዋነኛ ተልዕኮ በያዘው ዓለም አቀፉ የጸጥታ ጥበቃ ድጋፍ ኃይል ስር የሚንቀሳቀሱ ናቸው። የመ
ፖሊሶቹ ይጓዙበት የነበረውና በጣም አደገኛ የሚባለው አካባቢ የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን ኔቶ በሚመራውና በምህጻሩ አይዛፍ እየተባለ በሚታወቀው ዓለም አቀፉ የጸጥታ ጥበቃ ድጋፍ ኃይል ቁጥጥር ስር ይገኛል። በየቀኑ ብዙ ተሽከርካሪዎች በሚተላለፉበትና የታሊባን ሚሊሺያዎች ተጠናክረው ይንቀሳቀሱበታል በሚባለው በዚሁ አካባቢ የፓሽቱን ጎሳ አባላት የሚኖሩ ሲሆን ብዙዎቹ የታሊባን ደጋፊዎች እንደሆኑ ይነገራል። እነዚሁ የታሊባን ደጋፊዎችም ከመዲናይቱ ካቡል ወደ ጃላላባድ በሚወስደውና በርካታ የጦር ሰፈሮች በሚገኙበት መንገድ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ለመጣል አቅደዋል ሲል የካቡል ፖሊስ አስታውቋል።>የጀርመን መንግስት ጥቃቱን ለማጣራት የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በማስታወቅ ለሟቾቹ ቤተሰቦች ሀዘናቸውን ገልጸዋል። የሶስቱ ጀርመናውያን ፖሊሶች መገደልን የጀርመን ፖለቲካ ፓርቲዎች በጠቅላላ ግድያውን ቢያወግዙም፡ ሀገራቸው በአፍጋኒስታን የምታደርገውን ትብብር እንድታቋርጥ ምክንያት ሊሆን እንደማይገባ የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ የውጉም ቃል አቀባይ ጌርት ቫይስኪርኸ አስታውቀዋል።