1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሳውዲ ቀነ ገደቡን እንድታራዝም ጠየቁ 

ማክሰኞ፣ ሰኔ 20 2009

የሳውዲ አረብያ መንግሥት ሕገ ወጥ ያላቸዉን ስደተኞች ከሃገሩ እንዲወጡ የሰጠዉ ቀነ ገደብ ዛሬ ተጠናቆአል። እስካሁን ወደ ሃገራቸዉ ለመመለስ ከተመዘገቡ 110 ሺህ ኢትዮጵያዉያን 42 ሺዉ ብቻ መመለሳቸዉን የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ቀባይ ጽ/ቤት ገልፆአል።

https://p.dw.com/p/2fUI1
Äthiopien Ministerpräsident Hailemariam Desalegn
ምስል Getty Images

Ber. A.A.(PMHD fordert die saudische Reg.auf Fristverlängerung) - MP3-Stereo

 

ጊዜ ገደቡ ሳይጠናቀቅ ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ካለዉ የተመላሽ ቁጥር አንፃር ፣ ቀነ ገደቡ እንዲራዘም ለሳውዲ አረብያ መንግሥት ጥያቄ ማቅረባቸዉን እና ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከሳዉዲ በኩል ምላሽ አለመሰጠቱን ታዉቋል። 

ዩሃንስ ገብረእግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ