1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠብታ አምቡላንስ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 2004

አደጋ በደረሰበት ስፍራ የተገኘ ማንኛዉም ሰብዓዊነት የሚሰማዉ ግለሰብ ተጎጂዉን ለመርዳት ጥረት ማድረጉ የማይቀር ነዉ። አደጋ ለደረሰበት ሰዉ በዚያዉ ስፍራ የሚሰጠዉ የመጀመሪያ ርዳታ በተለይ ጉዳቱ የጠና ከሆነ ወሳኝ መሆኑን ባለሙያዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/15Uxv
ምስል Ssogras/Fotolia

ብዙዎች ስለህክምና ርዳታ ሲያስቡ አስቀድሞ የሚታያቸዉ ዶክተርና ሃኪም ቤት ነዉ። ደጋዉ በደረሰበት ስፍራ የሚሰጠዉ የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ አደጋዉ ከባድ ከሆነ የተጎጂዉን ነፍስ ለማትረፍ፤ ደም ፈሶ ከሆነም የማቆም እንዲሁም አቅም ከፈቀደ የመተንፈሻ አካላት በቂ ኦክስጂን እንዲያገኙ ማድረግን በማካተቱ ወሳኝነት ይኖረዋል። የመጀመሪያ ህክምና ርዳታ ሰጪዉ ሙያዊ ስልጠና ያለዉ ከሆነ ደግሞ ተጎጂዉን ከህልፈተ ህይወትም ሆነ በአደጋዉ ምክንያት ሊደርስ ከሚችልም የአካል ጉዳት መታደግ ይቻላል።

Österreich Unfalltod von Jörg Haider in Lambichl bei Klagenfurt
ምስል AP

ኢትዮጵያ ዉስጥ የግል የአምቡላንስ አገልግሎትን የጀመሩት አቶ ክብረት አበበ አደጋ የደረሰበትን ሰዉ ማንሳቱ ራሱ ሳይንስ እንደሆነ ነዉ የሚያስረዱት። ተጎጂዉን የማዳኑንም ተግባር እዚያዉ እንደሚጀምር ያስረዳሉ። ጠብታ አምቡላንስ በሚል የዛሬ ሶስት ዓመት በሶስት አምቡላንስ ሥራዉን የጀመረዉ ድርጅታቸዉ፤ ዛሬ የአምቡላንሱን ቁጥር አራት አድርሷል። አገልግሎቱም በዋና ከተማ አዲስ አበባ ብቻ ሳይወሰን በተፈለገበት ለርዳታ እንደሚደርስም ይናገራሉ። እንደምኞታቸዉ ቢሆን የአየር አምቡላንስንም ሀገሪቱ ማቅረብ ብትችል፤ ከጎረቤት ኬንያ፤ ደቡብ አፍሪቃም ሆነ ከሌሎች ሀገሮች የሚመጡ አገልግሎቶችን እዛዉ መስራት በተቻለ ይላሉ።

Piktogramm Erste Hilfe
ምስል picture-alliance/ ZB

በእሳቸዉ ዓላማና መነሳሳት የተቋቋመዉ ጠብታ የአምቡላንስ አገልግሎት ዛሬ ከአምስት በላይ ቋሚ ሠራተኞችንና ከአስር በላይ አማካሪዎችን ያካተተ ድርጅት ለመሆን መብቃቱንም አቶ ክብረት አበበ ገልፀዉልናል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ