ጠብመንጃ በየጓዳው
ሐሙስ፣ መጋቢት 10 2001ማስታወቂያ
የአስራ ሰባት ዓመቱ ወጣት በአባቱ ጠመንጃ የአስራ አምስት ሰዎችንና የራሱን ህይወት ካጠፋ ወዲህ መሰል አሰቃቂ ግድያዎችን መከላከያው መንገድ ምን መሆን አለበት የሚለው ጥያቄ ከየአቅጣጫው እየተሰነዘረ ነው ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ከሚመለከታቸው ነጥቦች ውስጥ ቀዳሚው ነው ። ከአውሮፓ መንግስታት አንዳንዶቹ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በስደተኞች አያያዝ እየተተቹ ነው ። ከነዚህም ውስጥ የፈረንሳይ መንግስት ሲገኝበት በተለይ ካሌ በተባለው የሰሜናዊ ፈረንሳይ የወደብ ከተማ የስደተኞች ሁኔታ ይበልጡን ይወቀሳል ። በዚህች ከተማ በኩል ወደ ብሪታኒያ የገቡ ስደተኞች እንደሚናገሩት የወደብ ከተማዋ ካሌ የስደተኞች የቁም ስቃይ መቁጠሪያ ስፍራ ናት ። ካሌን አልፈው ብሪታኒያ የገቡ ያሳለፉትን መከራ እንዲሁም በብሪታኒያ የስደተኞች ይዞታን የሚያስቃኝ ዝግጅትም አለን ።
DW,Spiegel online ,AFP ,DPA
ሒሩት መለሠ
ሸዋዬ ለገሠ