ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰጡት ማብራሪያ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 2 2001ማስታወቂያ
ብዙዎቹ ጥያቄዎች በሶማልያ፡ ብሎም፡ የኢትያጵያ መከላከያ ሰራዊው ከዚያ ይወጣል በተባለበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነበሩ፤ ይሁንና፡ በርካታ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ፡ ለምሳሌ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና መገናኛ ብዙኃን መንግስታቸውን አዘውትረው የሚወቅሱበት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ፡ የፊናንሱ ቀውስ፡ የምግብ ዋጋ ንረትና ግሽበትን የመሳሰሉ ጥያቄዎችም ተነስተው ነበር። ታደሰ እንግዳው