1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጎርፍ እና አርብቶ አደሩ

Merga Yonas Bulaሰኞ፣ ሐምሌ 4 2008

የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት «ፋኦ» ባለፈው ማክሰኞ ባወጣዉ ዘገባ በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ጎርፍ በአርብቶ አደሩ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱንን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/1JLwV
Pastoralisten Somalia
ምስል DW/J.Jeffrey

[No title]

በዚሁ በኦሮሚያ፣ በዱቡብ ክልል፣ በአፋር፣ በሶማሊያ እና በአማራ ክልል በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከ55,000 ሄክታር በላይ መሬት፣ ከጥቅም ዉጭ መሆኑን ዘገባዉ ያትታል። ከዚህ መሬት ውስጥ ደግሞ አብዛኛው የግጦሽ መሬት ነው።

በኢትዮጵያ በተከሰተዉ ድርቅ ግንባር ቀደም ተጠቂ በሆነው በአርብቶ አደሩ አካባቢ የጎርፍ አደጋ የቀንድ ከብቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰ ሮም የሚገኘው የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በ«ፋኦ» የአገሮችእና የህዝቦች ጥንካሬ መጎልበቻ ክፍል ሃላፊ ዶክተር ሹክር አህመድ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ መንግስት አርብቶ አደሮቹን ለመርዳት ብዙ ስራዎች ኢየተሰሩ መሆኑን እና ለክረምቱም ቅድመ ዝግጅቶች ኢዒ,ተደረጉ መሆኑን የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘዉዴን ይናገራሉ።

በጎርፍ ምክንያት ፣ የ77, 118 አባዋራዎች ፣ 1.4 ሚሊዮን ቀንድ ከብቶች ለሚያስፈልጋቸው ክትባት እና ሌሎች የጤና አገልግሎቶች ሦስት ሚልዮን ዶላር እንደምያስፈልገዉ «ፋኦ» በዘገባዉ አስታውቋል።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ