ግጭትና መፍትሄው ድራማ ክፍል 4
ረቡዕ፣ ጥቅምት 7 2005ማስታወቂያ
ግጭትና መፍትሄ ላይ በሚያተኩረውና “እንዳባቶቻችን” በተሰኘው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ክፍል አራት ላይ ደርሰናል፡፡ ባለፈው ሳምንት ዝግጅታችን ከሁለት የተለያዩ ጎሳዎች የሆኑት ማሳምቦና ሚቱምባ ቤተሰባቸውን ለመመገብ ተፈጥሮ ላይ በየፊናቸው ባደረጉት ርብርብ በመካከላቸው ውስጣዊ ግጭት አይሎ ነበር፡፡ ሚቱምባ የማሳምቦ ከብቶች ከወንዙ እንዳይጠጡ ካከላከሉ በኋላ ማሳምቦ ከብቶቻቸውን የሚቱምባ ማሳ ላይ ነድተዋል፡፡ ሁለቱም ለችግሩ መንስኤ አንዱ አንዱ ላይ ጣቱን በመቀሰር ከየጎሶቻቸው ርዳታ ፍለጋ ተጉዘዋል፡፡ ይህ ግጭት ይወገድ ይሆን? የሚወገድ ከሆነስ በምን መልኩ ነው የሚወገደው? የዛሬውን “እድለ-ቢስ ጀግኖች” የተሰኘውን ክፍል ይከታተሉ፡፡ ሌላና ሻኒ የወደመ ማሳቸውን ሲመለከቱ በድንጋጤ ወደ ደነዘዙበት ክስተት እናመራለን፡፡