ግብጻውያን ወጣቶች እና ተቃውሟቸው2 ኅዳር 2003ሐሙስ፣ ኅዳር 2 2003የተማሩ ናቸው፡ ጥሩ ስራ እና ጥሩ የወደፊት ዕድል አላቸው። ለነገሩ በግብጽ የመንግስቱ ተቃዋሚ የሆኑት ወጣቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ብዙ ጥቅም ስለሚያገኙ አትራፊ ናቸው ሊባሉ ይችላል፤ ሆኖም፡ ደስተኞች አይደሉምhttps://p.dw.com/p/Q6Ghምስል dpaማስታወቂያየሙባራክ ትውልድ እየተባሉ የሚጠሩት ወጣቶች ሌላ ፕሬዚደንት አይተው አያውቁም። የሚመሩት በአያቶቻቸው ዕድሜ በሚገኙ ባለስልጣናት ሲሆን፡ በሀገራቸው ጉዳይ ውስጥ የመናገር ዕድል አላጋጠማቸውም። ምንም እንኳን የማስፈራራቱን ተግባር ስራየ ብሎ የተያያዘውን የሀገሪቱን መንግስት ባያደስትም አሁን ይህ እንዲለወጥ እና መብታቸው እንዲከበር አደባባይ ወጥተዋል። ኤስተር ሳውብ አርያም ተክሌ ሂሩት መለሰ