1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግብረ ሰናይ ሰራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በሶማሊያ

ሰኞ፣ ጥቅምት 10 2001

ባሳለፍነዉ ሳምንት በሶማሊያ በተከታታይ የተሰነዘሩት ጥቃቶች ሁለት የግብረ ሰናይ ባልደረቦችን ህይቀት ቀጥፈዋል።

https://p.dw.com/p/Fdh1
ተሰዉሮ ጥቃት ማድረሱ ተለምዷል
ተሰዉሮ ጥቃት ማድረሱ ተለምዷልምስል AP

የተመድ የዓለም የምግብ ድርጅት WFP ባልደረባ ባለፈዉ ዓርብ ሲገደል እሁድ ዕለት ደግሞ የመንግስታቱ የህፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF አንድ አባሉን በተመሳሳይ ድርጊት ማጣቱ ተሰምቷል። ጽሕፈት ቤቱ ኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ የሚገኘዉ UNICEF SOMALIA ግድያዉን እያጣራ መሆኑን ገልጿል። የሶማሊያ ዳግም ነፃ አዉጪ ግንባር ግድያዉን አዉግዞ የዉጪ ወራሪዎች በአገሪቱ መገኘታቸዉን ለድርጊቱ ተጠያቂ አድርጓል።