1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግርክ ከአበዳሪዎቿ ብድር ታገኝ ይሆን?

እሑድ፣ ሐምሌ 5 2007

የግሪክ የብድር ጉዳይ እስካሁን መጨረሻ አላገኘም። የዮሮ ቡድን ሀገራት እስካሁን የግሪክን የብድር ጥያቄ አስመልክቶ የጋራ ነጥብ ላይ ሊደርሱ አልቻሉም።

https://p.dw.com/p/1FxXJ
Brüssel EU Regierungsgipfel zu Griechenland Tsipras Juncker Hollande Michel
ምስል picture-alliance/AP Photo/G. V. Wijngaert

ግሪክ ተጨማሪ ብድር እንድታገኝ ያቀረበችው አዲስ የቁጠባ ዕቅድ ላይ ለመደራደር ቤልጄም-ብራስልስ ውስጥ ጉባኤ የያዙት የዩሮ ሸርፍ አባል ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች ለግሪክ ቀውስ የ19ኙ ሃገራት መራሔ መንግሥታት እና ጠቅላይ ሚንስትሮች መፍትኄ እንዲፈልጉ አሳሰቡ። «እጅግ ወሳኝ የሆኑ ጥያቄዎች አሁንም ድረስ መልስ አላገኙም» ሲሉ የዩሮ ቡድኑ መሪ ጄሮዬን ጄዜልብሎም ዛሬ ከብራስልስ አስታውቀዋል። ለግሪክ ቀውስ መፍትኄ ለማበጀት በጥቂት ቀናት ለሁለተኛ ጊዜ በአስቸኳይ የተጠራው ልዩ ጉባኤ ላይ የቀረበው ሐሳብ ከገንዘብ ሚንስትሮች በላይ ስለሆነ ለመፍትኄ ወደ መሪዎች መተላለፉ ተጠቅሷል። የግሪክ ጠቅላይ ሚንሥትር አሌክሲስ ሲፕራስ «ከልብ ለሆነ ድርድር» ዝግጁ ነኝ ሲሉ ተደምጠው ነበር። የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲባል ብቻ አዲሱን የግሪክ የቁጠባ ዕቅድ እንደማያፀድቁ አስጠንቀዋል። ፈረንሣይ እና ጣሊያን ጀርመን አቋሟን ለዘብ ታድርግ ሲሉ ጠይቀዋል። የግሪክ መንግሥት ከባድ የገንዘብ ክስረት የደረሰበት ሲሆን፤ ሀገሪቱ ባለፉት ወራት ለአበዳሪዎች 4,2 ቢሊዮን ዩሮ ዕዳ መመለስ ነበረባት። በውይይቱ ወቅት ግሪክ ከገባችበት ቀውስ ለመውጣት የ72 ቢሊዮን ዩሮ ርዳታ መጠየቋ ተዘግቧል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ