1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዛ ከጦርነቱ በኋላ

ሐሙስ፣ ጥር 14 2001

የጋዛ ሲቭል ህዝብን ስቃይ ለማቃለል ይቻል ዘንድ እስራኤል ከጋዛ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ለሰብዓዊ ርዳታ አቅርቦት መተላለፊያ መክፈትዋን

https://p.dw.com/p/GeK2
ሲፒ ሊቭኒ
ሲፒ ሊቭኒምስል AP

ትናንት በብራስልስ ከአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ጋር የተወያዩት እስራኤላዊት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሲፒ ሊቭኒ አስታውቀዋል። በእስራኤል የሶስት ሳምንት ጥቃት በጋዛ ከሞተው ሰው ጎን የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው እጅግ ብዙ ፍልስጤማውያን እስካሁን ተገቢውን ህክምና ማግኘት አልቻሉም። እና የአውሮጳ ህብረት ከሊቭኒ ጋር ባደረገው ውይይት ይኸው የፍልስጤማውያኑ ሁኔታ የሚሻሻልበትን ዜዴ ለማፈላለግ ሞክሮዋል።