ጉባኤ ና ተቃውሞ በአሜሪካ
ሰኞ፣ የካቲት 18 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት 2 ተኛ ጉባኤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቨርጂኒያ አሜሪካን ውስጥ ተካሄደ ። ጉባኤው የምክር ቤቱ ን የእስካሁኑ እንቅስቃሴ መገምገሙንና የወደፊት አቅጣጫውንም ማስተዋወቁን የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ዘግቧል ። በሌላ በኩል በዋሽንግተን ዲሲ ና አካባቢዋ በሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሙስሊሞች አስተባባሪነት ባለፈው ቅዳሜ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሰልፍ ተካሄዷል ። ስለ ቨርጂኒያው ጉባኤ ና ስለ ዋሽንግተን ዲሲው ሠላማዊ ሠልፍ አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ