1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጉራማይሌ በቋንቋችን ለምን አስፈለገ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 20 2000

በተለያዩ የጀርመን የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአፍሪቃ የሚነገሩ ቋንቋዎች ላይ ጥናት ይካሄዳል ። ከነዚህ በአፍሪቃ ከሚነገሩ ቋንቋዎች መካከል በተለይ የአማርኛ የግዕዝ የኪስዋሂሊ እና የሃዉሳ ቋንቋ በዩንቨርስቲ ዉስጥ እንደ አንድ ጥናት ዘርፍ ትምህርት ይሰጥበታል

https://p.dw.com/p/E0lu
በሃንበርግ ላይፕሲግ እና ማይንዝ በተሰኙት የጀርመን ከተሞዎች ዉስጥ በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ደግሞ አማርኛ እና ግዕዝ ቋንቋን ጠንቅቀዉ የሚናገሩ የሚያነቡ እንደዚሁም የሚጽፉ ጀርመናዉያን ምሁሮች ይገኛሉ። አማርኛን ጠንቅቀዉ ሲናገሩ የራሳቸዉንም ሆነ ሌላ የባዕድ ቃል ሳይቀላቅሉ ሃሳባቸዉን በትክክል መግለጽ ይችላሉ። በርካታ ኢትዮጽያዉያን አማረኛ ተናጋሪዎች ግን ሃሳባችንን ኤክስፕሪስ ማድረግ ዲፊካልት ሲሆንብን ይታያል። እዚህ ላይ ፕሮብሌሙ ምን ይሆን። አማርኛችን ኢነፍ ቃላት ሳይኖረዉ ቀርቶ ነዉ? የኢትዮጽያ የስነ-ጽሁፍ እድገትስ ምን ይመስላል በሚለዉ ርእስ ዙርያ የዛሪዉ የባህል መድረካችን ከአዲስ አበባ በአማረኛ ቋንቋ ስር ከከጀርመናዉያን አቻዎቻቸዉ ጋር ጥናት ሊያደርጉ በእንግድነት ወደ ጀርመን ብቅ ብለዉ የነበሩ ምሁርን ይዞ ይቀርባል። መልካም ቆይታ