1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ገጣሚ-ምንተስኖት ማሞ

እሑድ፣ መጋቢት 4 2008

በሒሳብ እና በመዝገብ ሥራ የተሰማራ ቢሆንም ሥነ-ጽሑፍ መዝናኛዉ ፤ ከወዳጆቹ ጋር መገናኛዉ፤ በፈረንጆቹ አባባል ሆቢዉ ነዉ። የሥነ-ጽሑፍ ባልንጀሮቹ የእሱን ግጥሞች ያደመጡ ሁሉ ብዕሩ ረቂቅ መሆን ይመሰክሩለታል።

https://p.dw.com/p/1IBv6
Mentesenot Tadele
ምስል privat

[No title]

እሱ ራሱ ግን ስለሚጽፋቸዉ ሥነ-ግጥሞች ብዙም ማዉራት እንደማይችል፤ ባይሆን የጻፍኳቸዉን ላንብብላችሁ ሲል እንደሚጠይቅ ይናገራል። ምንተስኖት ማሞ ይባላል፤ የሥነ ግጥም ዝንባሌ ያደረበት ገና የሦስተኛ ክፍል ተማሪ እንደሆነ ይናገራል። ገጣሚ ምንተስኖት ማሞ ሥለ ራሱም ሆነ በሥነ-ግጥም ምሽት ዝግጅት ላይ ሥለሚያቀርባቸዉ ግጥሞች ቀደም ሲል እንደነገረን ሳይሆን በደንብ በዝርዝር ነዉ ገልፆልናል። በአዲስ አበባ በጎተ ተቋም በፑሽኪን አዳራሽ እንዲሁም በጃዝ የግጥም ምሽት ገጣሚ ምንተስኖት ግጥሙን ለአድማጭ ጆሮ የሚያደርስባቸዉ መድረኮች ናቸዉ። ባለፈዉ ዓመት በግጥም በጃዝ ምሽት ላይ ካቀረባቸዉና ተወዳጅነትን ካገኘበት ግጥሞቹ መካከል «የጫማ ምልከታ» የተሰኘዉ ግጥምም ተጠቃሽ ነዉ። ገጣሚ ምንተስኖት ማሞ ከዶይቼ ቬለ ጋር ያደረገዉን ሙሉዉን ቃለ መጠይቅ የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።


አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ