1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

በገቢ መጠን የሚወሰነው የድሕነት ልክ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 23 2010

በዓለም ባንክ ብያኔ መሰረት የቀን ገቢዎ ከ1.90 ዶላር በታች ከሆነ በከፋ ድኅነት ውስጥ እየኖሩ ነው። በኢትዮጵያ 52 ብር ገደማ ማለት ነው።

https://p.dw.com/p/2mw1N
Ökologische Nachhaltigkeit Trinkwasser Millennium Development Goals
ምስል AP

የዓለም ባንክ የድሕነት ትንታኔ

በዓለም ባንክ ብያኔ መሰረት የቀን ገቢዎ ከ1.90 ዶላር በታች ከሆነ በከፋ ድኅነት ውስጥ እየኖሩ ነው። በኢትዮጵያ 52 ብር ገደማ ማለት ነው። በባንኩ መረጃ መሰረት 767 ሚሊዮን ሰዎች የቀን ገቢያቸው ከ52 ብር በታች ነው። ለእነዚህ በከፋ ድሕነት ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች የቀን ገቢያቸው የዕለት ምግብ ለመሸመት ይውላል። ገቢያቸው የተመጣጠነ ምግብ ለመሸመት በቂ አይደለም። ጥራቱን የጠበቀ መኖሪያ ቤት የላቸውም፤ ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል ለቤተሰቦቻቸውም ሆነ ለራሳቸው የጤና መድኅን መግዛትም አይችሉም። በከፋ ድኅነት ውስጥ የሚኖሩት ሚሊዮኖች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች ዜጎች ናቸው። ግማሽ ያክሉ ደግሞ ሕንድ፤ ናይጄሪያ እና ቻይናን በመሳሰሉ መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገሮች የሚኖሩ ናቸው። የዓለም ባንክ እንደሚለው በሐብታም አገሮች የድኅነት መለኪያ ከፍተኛ ሲሆን በደሐ አገሮች ደግሞ ዝቅተኛ ነው። ለዚህም ባንኩ የድህነት መደቦችን እንደ አዲስ ከፋፍሏል። 
እሸቴ በቀለ