ጃፓን የአቶም ኃይል ጉዳት
ሰኞ፣ መጋቢት 5 2003ማስታወቂያ
ንዝረቱን ተከትሎ በፉኩሽማ ቁጥር 3 የአቶም ኃይል አመንጪ አውታር ውስጥ ፍንዳታ ሲደርስ ወታደሮችን ጨምሮ 11 ሰዎችም ተጎድተዋል ። የአቶም ኃይል ማመንጫውን የሚያስተዳድረው የቶክዮ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው የመሬት ንዝረቱ በተከሰተ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በኃይል ማመንጫው የሀይድሮጂን ጋዝ ፈንድቷል ። በዚሁ ማመንጫ የደረሰ ሁለተኛ ፍንዳታም የአንዱን የአቶም ማመንጫ አውታር አካል ከጥቅም ውጭ አድርጓል ።፡በርካታ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን እዚያ የሚቆዩትም ከቤታቸው እንዳይወጡ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ