ጂዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ11 ሐምሌ 2004ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 2004ስዑድ አረቢያ ጂዳ የሚኖሩ ወደሶስት መቶ የተገመቱ ኢትዮጵያዉያን የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ባለፈዉ ሳምንት ዓርብ በአወሊያ መስጊድ በተሰባሰቡ ሙስሊም ምዕመናን ላይ ተፈፀመ በተባለዉ የኃይል ርምጃ ማዘናቸዉን ገልጸዋል። እዚያ በሚገኘዉ ቆንስላ ግቢhttps://p.dw.com/p/15Zpbማስታወቂያ አዳራሽ በሳምንቱ ማለቂያ ተሰባስበዉ የነበሩት እነዚህ ወገኖች ጥያቄያቸዉን ለመንግስት ባለስልጣናት ለማቅረብ ባደረጉት ጥረት ከቆንስላዉ ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋ አለመግባባት መፈጠሩንም የጄዳ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል። ተሰብሳቢዎቹ ስድስት ነጥብ የያዘ የአቋም መግለጫ ማዉጣታቸዉን ነብዩ ዘርዝሯል። ነብዩ ሲራክ ሸዋዬ ለገሠ ነጋሽ መሐመድ