ጀርመን-ዶርትሙንድ የገቡ ስደተኞች2 ጳጉሜን 2007ሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2007ከ 20 000 በላይ ስደተኞች ባለፉት ሁለት ቀናት በሐንጋሪ እና ኦስትሪያ በኩል አድርገው ደቡብ ጀርመን ገብተዋል። ዛሬም ሌሎች በሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች ደቡብ ጀርመን ሙኒክ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።https://p.dw.com/p/1GSJxምስል picture-alliance/dpa/M. Hitijማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio ሙኒክ የስደተኞቹ የመጀመሪያ የጀርመን መዳረሻ ብትሆንም፤ ተገን ጠያቂዎቹ ወደ ሌሎች የጀርመን ግዛቶች በአፋጣኝ ይዘዋወራሉ። በዚህም መሠረት ሁለት ባቡር ሙሉ ስደተኞች ባሳለፍነዉ ቅዳሜ ምዕራብ ጀርመን የምትገኘው ዶርትሙንድ ከተማ ገብተዋል። ዲርክ ፕላነርት በስፍራው ተገኝቶ የዘገበውን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው አጠናቅሮታል። ይልማ ኃይለ ሚካኤል ልደት አበበ አዜብ ታደሰ