ጀርመን፤ የድንበር ቁጥጥር ልትጀምር ነው
እሑድ፣ መስከረም 2 2008ማስታወቂያ
ጀርመን ድንበሯን ለስደተኞች ክፍት ካደረገች አንስቶ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች በኦስትሪያ በኩል አድርገው ጀርመን ገብተዋል። ትናንት ቅዳሜ እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ 12,200 ስደተኞች ጀርመን ገብተዋል።በሌላ ዜና በወቅታዊው የስደተኛ ቀውስ ሳቢያ ከኦስትሪያ የሚደረጉ የባቡር ጉዞዎች በሙሉ ወደ ጀርመን መግባት ማቆማቸውን የኦስትሪያ የባቡር ድርጅት ቃል አቀባይ ዛሬ ማምሻውን አስታወቁ።
ልደት አበበ
እሸቴ በቀለ