1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን እና የቀኝ አክራሪዎች የግድያ ወንጀል

ሰኞ፣ ኅዳር 4 2004

የጀርመን የሀገር አስተዳደር ሚንስትር ሃንስ ፔተር ፍሪድሪኽ፣ እያሠጋ የመጣውን የቀኝ አክራሪዎች(ኔዎ ናዚስ) ወንጀል በተመለከተ ፖሊስና የህግ አካላት ሁሉ በፌደራል ክፍላተ ሀገር ደረጃ የበለጠ ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/RwTf
ምስል picture-alliance/dpa

የፍትኅ ሚንስትርዋ ወ/ሮ ዛቢነ ሎይቶይሰር -ሽናረንበርገርም ፣ የህገ-መንግሥት ጠባቂው ክፍል አሠራር፣ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር እስከማሳሰብ ደርሰዋል። ጀርመን ውስጥ የቀኝ አክራሪዎች፣ እ ጎ አ ከ 1990 ዓ ም፤ አንስቶ ከ 100 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ገድለዋል። 16,000 ገደማ የሚሆን የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል። በተከታታይ ስለተፈጸሙ ግድያዎች ህዝብ ፤ የህግ አካላትና ፖለቲከኞች በጥሞና መነጋገራችው አልቀረም። በእርግጥ ምን እየተባለ ነው? ወደ እስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ፣ የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬው ነበር። በእርሱ መልስ እንጀምራለን።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ