ጀርመን አፍሪቃዊትዋ የምዕተ -ዓመቱ የታሪክ መስካሪ29 መስከረም 2007ሐሙስ፣ መስከረም 29 2007የ 90 ዓመትዋ ደራሲ ሩት ቫይስ እትብታቸዉ የተቀበረበት ሀገረ ጀርመንን የሚያዉቁት እጅግ በጥቂቱ ነዉ። በደቡብ አፍሪቃ ግን አዛዉንቷ በሥነ-ጽሑፍ ስራቸዉ እጅግ ታዋቂና የተከበሩ ናቸዉ፤ ምናልባትም ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ ሩት እጅግ ታዋቂዋና ብቸኛዋ የጀርመናዊት ጋዜጠኛ ናቸዉ ማለትም ይቻላል።https://p.dw.com/p/1DSERማስታወቂያ ደቡብ አፍሪቃ ኬፕታዉን የሚገኘዉ የአይሁዳዉያን ቤተ-መዘክር የ 90 ዓመቷን ጋዜጠኛ፤ ለማወደስ አንድ የህይወት ዘመን ታሪካቸዉን የሚያሳይ አዉደ- በማዘጋጀት ክብሩን ገልጾአል። የዕለቱ ዝግጅታችን ሥለ ጀርመን አፍሪቃዊትዋ የምዕተ -ዓመቱ የታሪክ መስካሪ ጥንቅር ይዞአል።