ጀርመን አንድነትና የህዝቡ ስሜት22 መስከረም 2000ረቡዕ፣ መስከረም 22 2000በአዉሮፓዉያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 3 ማለትም የዛሬዉ ዕለት ጀርመን ከሁለትነት ወደአንድነት ተሸጋግራ የተዋሃደችበት 17ኛ ዓመት ነዉ።https://p.dw.com/p/E0buበዓሉ ሲከበርምስል APማስታወቂያ ከምስራቅና ምዕራብ ዉህደት በኋላ በርግጥም የምጣኔ ሃብት እድገቱ በምስራቁ ምድር ከፍ ብሎ ታይቷል። የስራ አጡም ቁጥር ቀንሷል። ጀርመኖች በጋራ መስራት ጀምረዋል፣ ምንም እንኳን ከአዉሮፓዉ ደረጃ ምስራቃዊዉን የአገሪቱን ክፍል ለማስተካከል በርካታ ገንዘብ ለማፍሰስ ቢገደዱም። እንድገቱ ግን እንዳሰቡት ቶሎ የሚታይ አልሆነም።