ጀርመን ለሊቢያ አማፅያን እዉቅና ሰጠች
ሰኞ፣ ሰኔ 6 2003ማስታወቂያ
የብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት የፖለቲካ አማካሪ ና የውጭ ጉዳዮች ቃል አቀባይ አህመድ ጂብሪል ለዶቼቨለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት የሊቢያው ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ብሔራዊ የሽግግር ምክርቤት በተባበሩት መንግሥታት አማካይነት ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ጋር እየተነጋገረ ነው ። ከተለያዩ መንግሥታት እውቅና ያገኘው ብሔራዊው ምክር ቤት በሊቢያ የወደፊት ዕጣ ላይ የሚመክር ሰፊ ጉባኤ በማዘጋጀት ላይ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ