ጀርመን:መርዛማዉ የከብቶች መኖና ሥጋቱ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 28 2003ማስታወቂያ
መርዛማዉ የከብቶች መኖና ሥጋቱ
ጀርመን ዉስጥ የዶሮና የሌሎች እንስሳት መኖ የሚያዘጋጁ ፋብሪካዎች ከመኖዉ ጋር መርዛማ ንጥረ ነገር መቀላቀላቸዉ የሐገሪቱን ፖለቲከኞችና እንስሳ አርቢዎችን አስቆጥቷል።ከመኖዉ ጋር የተቀላቀለዉ ዳዮክሲን ወይም በጀርመንኛዉ ዲዮክሲን የተባለዉ መርዛማ ንጥረ ነገር በተለይ እንቁላልና ሥብ ሥጋ የሚመገቡ ሰዎችን ለአደገኛ ነቀርሳ ወይም ካንሰር እንደሚዳርግ የጤና ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።ጉዳዩ ባደባባይ መነገር ከጀመረበት ጀምሮ አብዛኛዉ ሕዝብ እንቁላልና ሥጋ መመገቡን አቁሟል።ይሕ ደግሞ እንስሳ አርቢዎችንና ነጋዴዎች እያከሰረ ነዉ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝርዝሩን ልኮናል።
ይልማ ሐ/ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ