1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመናውያንና ሳይንሳዊ ያልሆኑ ባህላዊ እምነቶቻቸው፣

ረቡዕ፣ ግንቦት 4 2002

አፍሪቃዊ፣ እስያዊ፣ አውሮፓዊም ሆነ አሜሪካዊ፣ የሰው ልጅ በአጠቃላይ፣ ሳይንሳዊ መረጃ የሌላቸውን ልማዳዊ እምነቶች የሙጥኝ የሚለው፣ ተፈጥሮው፣ የፍርሃት ተገዥ ስላደረገው ሳይሆን አልቀረም።

https://p.dw.com/p/NMPV
በጀርመንና በሌሎችም አገሮች ገደ-ቢስ የሚሰኘው ቁጥር፣ 13ምስል picture-alliance/Bildfunk

ሰው፣ በተለይ ለማያውቀው፣ ተመራምሮም ገና ምላሹን ላላገኘለት ጉዳይ፣ የራሱን ግምትም ሆነ መላ-ምት በማስቀመጥ፣ አመክንዮ በሌላቸው የተለያዩ ልማዳዊ እምነቶችን የመቀበል አዝማሚያ ይታይበታል።

አስማት፣ ጥንቆላ፣ ሳይንሳዊ መረጃ የሌለው እምነት ፣ እነዚህ ሁሉ፣ እስከዛሬ ድረስ በዕለት-ተዕለት ባህላዊ እንቅሥቃሤ ቦታ አላጡም። ሰይጣን፣ ርኩሳን መናፍስት፣ መላእክትና ተረታዊ ታሪኮች፣ የሰው፣ የማይወገዱ የባህሉ አካላት ሆነው ቀጥለዋል። መጥፎም ሆነ ጥሩ ገድ፣ በሚባሉ ምልክቶች የማመኑና የመጠራጠሩ አባዜ ፣ የሥነ-ልቡና ጠበብት እንደሚሉት፣ የሰው ልጅ ያለመርካት ውጤት ሲሆን፣ ይህ ራሱ ከራሱ፣ ከሰው ፍጥረትና አብሮ ከመኖር ባህል ጋር ተሣሥረው የዘለቁ ናቸው።

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ፣