1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመናውያኑ ታጋቾች አዲስ አበባ ገቡ

ዓርብ፣ የካቲት 30 2004

ጥር 9 ቀን 2004 ዓ ም ከአፋር ታግተው ከተወስዱ በኋላ ባሳለፍነው ሰኞ መለቀቃቸው የተነገረው ሁለት ጀርመናውያን ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል ። ጀርመናውያኑ አገር ጎብኝዎች ትናንት በአፋር የሃገር ሽማግሌዎች ታጅበው ከበርሃሌ

https://p.dw.com/p/14ITQ
ምስል picture-alliance/dpa


ጥር 9 ቀን 2004 ዓ ም ከአፋር ታግተው ከተወስዱ በኋላ ባሳለፍነው ሰኞ መለቀቃቸው የተነገረው ሁለት ጀርመናውያን ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል ። ጀርመናውያኑ አገር ጎብኝዎች ትናንት በአፋር የሃገር ሽማግሌዎች ታጅበው ከበርሃሌ በሄሊኮፕተር መቀሌ እንደደረሱ በመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ የጀርመን ኤምባሲ ተወካዮች እንደተረከቧቸው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ። ጠለፋው በኤርትራ ቀጥተኛ ተሳትፎ ተፈጽሟል የምትለው ኢትዮጵያ ፣ የአፋር ሽማግሌዎች ባደረጉት ጥረትና በኢትዮጵያ መንግሥት ትብብር ጀርመናውያኑ በመለቀቃቸው መደሰቷን ገለፃለች ። እጣ ፈንታቸው እስካሁን ያልታወቀው ከነርሱ ጋር የተጠለፉትን 2 ኢትዮጵያውያንን ለማስፈታት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያው ጥረት እንደምትገፋም አሰታወቃለች ። ዮሐንስ ገብረ እግዚ አበሔር

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አበሔር
ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ