ዶክተሮቿን ያጣችዉ አፍሪቃ3 መጋቢት 2000ረቡዕ፣ መጋቢት 3 2000የዓለም የጤና ድርጅት ወደአራት ሚሊዮን የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች የዓለም ህዝብ የጤና ይዞታ ለማስተካከል እንደሚያስፈልጉ ይገልፃል።https://p.dw.com/p/E0mZየሃኪም ያለህ...... (በደቡብ አፍሪቃ)ምስል picture-alliance / dpa/dpawebማስታወቂያከደቡብ አፍሪቃ አገራት ብቻ 10ሺ ዶክተሮች አገሮቻቸዉን ትተዉ ወይ አሜሪካ ወይ አዉሮፓ አለበለዚያም ህንድ ወስጥ እየሰሩ ናቸዉ። ኢትዮጵያን ስንወስድ ደግሞ አገሪቱ ወስጥ ከሚገኙት የጤና ዶክተሮች ይልቅ በአሜሪካ በመስራት ላይ ያሉት በቁጥር እንደሚበልጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የብሪታኒያዉ የህክምና መፅሄት እንደሚለዉ በአሜሪካ ለ1,000 ሰዎች ከዘጠኝ በላይ የሚሆኑ ነርሶች ይደርሳሉ፤