1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድጋፍና ተቃውሞ በግብፅ

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2005

በግብፅ ፕሬዝዳንታዊ ቤተመንግስት ፊት ለፊት የተጋጩት የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎች አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ የግብፅ የክብር ዘብ ዛሬ ትዕዛዝ ካስተላለፈ በኋላ የሙርሲ ደጋፊዎች ከስፍራው እንደለቀቁ ተዘገበ ። ይሁንና ሙርሲ ያወጡትን ድንጋጌ በመቃወም የተሰበሰቡት ሰዎች ተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ዝተዋል ።

https://p.dw.com/p/16x0Q
Egyptian Army tanks deploy near the presidential palace to secure the site of overnight clashes between supporters and opponents of President Mohammed Morsi in Cairo, Egypt, Thursday, Dec. 6, 2012. The Egyptian army has deployed tanks outside the presidential palace in Cairo following clashes between supporters and opponents of Mohammed Morsi that left several people dead and hundreds wounded. (Foto:Nasser Nasser/AP/dapd)
ምስል AP

በግብፅ ፕሬዝዳንታዊ ቤተመንግስት ፊት ለፊት የተጋጩት የግብፁ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎች አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ የግብፅ የክብር ዘብ ዛሬ ትዕዛዝ ካስተላለፈ በኋላ የሙርሲ ደጋፊዎች ከስፍራው እንደለቀቁ ተዘገበ ። ይሁንና ሙርሲ ከ 2 ሳምንት በፊት ያወጡትን ድንጋጌ በመቃወም ቤተ መንግሥቱ አካባቢየተሰበሰቡት ሰዎች በተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ዝተዋል ። ሙርሲ ማምሻውን ለህዝቡ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

Egyptian riot police stand guard during clashes between supporters and opponents of Egyptian President Mohammed Morsi outside the presidential palace in Cairo, Egypt, Wednesday, Dec. 5, 2012. Supporters and opponents of Egyptian leader Mohammed Morsi fought with rocks, firebombs and sticks outside the presidential palace in Cairo on Wednesday in large-scale clashes that marked the worst violence of a deepening crisis over the disputed constitution. (AP Photo/Mostafa Elshemy)
ምስል dapd

የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ብዙ ሥልጣን የሚያሰጣቸውን ተቃውሞ ያስነሳ ድንጋጌ ካወጡ 2 ሳምንት ሞላው ። ያኔ ድንጋጌውን በመቃወም ታህሪር አደባባይ የተጀመረው አመፅ ወደ ፕሬዝዳንታዊው ቤተ መንግሥት ተሸጋግሮ ግጭቱ በፖሊስና በሰልፈኞች መካከል መሆኑ ቀርቶ በተቃዋሚዎችና በደጋፊዎች መካከል ከሆነ 2 ቀናት ተቆጥረዋል ። ሆኖም ዛሬ የግብፅ የክብር ዘብ በፕሬዝዳንታዊው ቤተ መንግሥት አካባቢ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድን በማገድ ሰልፈኞቹም አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ ባዘዘው መሠረት የሙርሲ ደጋፊዎች የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከመድረሱ በፊት ጓዛቸውን ጠቅለው ሲነሱ ተቃዋሚዎች ግን እዚያው ቀርተዋል ። በቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት ሲጋጩ ውለው ያደሩትን የሞርሲ ተቃዋሚ ደጋፊዎች ለመለየትም የክብር ዘቡ ታንኮች መሃላቸው እንዲቆም ማደረጉን ሃላፊው ጀነራል ሞሐመድ ዛኪ አስታውቀዋል ። ተቃዋሚዎች ግን ቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት ሌሎች የተቃውሞ ሰልፎችን ማካሄዳቸው እንደማይቀርም እየዛቱ ነበር ቀን ። ተቃዋሚዎች ሙርሲ ከሥልጣን ይውረዱ ፤ ረቂቅ ህገ መንግሥቱም ይቀየር ነው የሚሉት ።

An anti-Mursi protester shouts during a protest against the president outside the presidential palace in Cairo December 5, 2012. Islamists fought protesters outside the Egyptian president's palace on Wednesday, while inside the building his deputy proposed a way to end a crisis over a draft constitution that has split the most populous Arab nation. REUTERS/Mohamed Abd El Ghany (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል Reuters

«ሙርሲ በእውነት አያስፈልጉንም።እርሳቸው እንዲመሩን አንፈልግም። የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበርንም አንፈልግም፤ ረቂቅ ህገ መንግሥቱ እንዲቀየር ነው የምንፈልገው »

Paramedics help injured anti-Mursi protesters, who according to supporters of the Muslim Brotherhood have been detained by supporters of the brotherhood during clashes between supporters and opponents of Mursi, outside the Egyptian presidential palace in Cairo December 6, 2012. At least three tanks are deployed outside the palace on Thursday in a street where supporters and opponents of President Mohamed Mursi had been clashing into the early hours of the morning, a Reuters witness said. REUTERS/Asmaa Waguih (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል Reuters

ከ 9 ቀን በኋላ ለህዝበ ውሳኔ ይቀርባል የተባለውን ረቂቅ ህገ መንግሥት  ለዘብተኞችና ክርስቲያኖች አልተቀበሉትም ። ለፕሬዝዳንት ሞርሲ ፍርድ ቤት ሳይቃወማቸው እርምጃ መውሰድ የሚያስችላቸው ሥልጣን የሚሰጠውን ድንጋጌ ከወጣ በኋላ በተከሰተው ብጥብጥ መንስኤ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 7 ደርሷል ። ከመካከላቸው 5 ቱ ትናንትናና ከትናnte በስተያ ተጠናክሮ በቀጠለው በተቃዋሚዎችና ደጋፊዎች ግጭት ነው የተገደሉት ። በግጭቱ ሰበብ 4 የሙርሲ አማካሪዎች እንዲሁም የግብፅ መንግሥታዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሃላፊ በፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸው ተዘግቧል ። ትናንት በ 10 ሺህዎች የሚቆጠሩ በቤተ መንግሥቱ ፊት ለፊት ተቀምጠው የነበሩ ተቃዋሚዎችና የሙርሲ ደጋፊዎች ተቀጣይ ፈንጂና ድንጋይ ሲወራወሩ መኪናዎችም ሲያቃጥሉ ነው ያመሹት ። የካይሮው ብጥብጥ ለሊቱን ወደ ወደብ ከተማዋ ኢስማይሊያ ና ስዌዝ ተዛምቶ ተቃዋሚዎች የሙስሊም ወንድማማቾች ማህበርን ቢሮዎች አቃጥለዋል ።

ምዕራባውያን መንግሥታት የግብፁ ግጭት በውይይት እንዲፈታ እየጠየቁ ነው ። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን ችግሩን ለመፍታት ግልፅና ዲሞክራሲያዎ ውይይት እንዲካሄድ ጠይቀዋል ።  የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተር ቬለም ሁሉም ወገኖች ለችግሩ ሠላማዊ መፍትሄ እንዲሹ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

« ከካይሮ በሰማሁት ዜና እጅግ ተደናግጫለሁ። አመፅ ለሃገር ውስጥ የፖለቲካ አለመግባባቶች የኃይል እርምጃ መፍትሄ አይደለም ። ሁሉም ወገኖች በሰከነ መንፈስ በማስተዋል ለችግሩ መላ እንዲፈልጉለት እማፀናለሁ »

ምንም እንኳን ተቃውሞው ቢቀጥልም የግብፅ ምክትል ፕሬዝዳንት መሐመድ ሜኪ ሂሻም በረቂቅ ህገ መንግሥቱ ላይ የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል ። ሂሻም ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉም ብለዋል ። ብጥብጡ ከተባባሰበት ጊዜ አንስቶ ከመገናኛ ብዙሃን የራቁት ሞርሲ ዛሬ ማምሻውን በቴሌቪዥን ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ