1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድርቅና የምግብ ዕጥረት በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 9 2000

አፍሪቃውያን የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ዕርዳታ ጠባቂ ከመሆን ይልቅ ራሳቸውን ችለው እንዲያድሩ ተጠየቁ ።

https://p.dw.com/p/EdjV
ዝናብ ያጠረው መሬት
ዝናብ ያጠረው መሬትምስል AP

ኢትዮጵያና ኬንያን የጎበኙት የጀርመንና የላክሰምበርግ ኬር ሊቀመንበር ሄርበርት ሻርንብሩህ ዛሬ ከዶይቼ ቬለ ጋራ ባካሄዱት ቃለምልልስ እንደተናገሩት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ድርቅ በተደጋጋሚ የሚያጠቃቸው ሀገራት ካለፉት ዓመታት ልምድ በመነሳት በመጪዎቹ ዓመታት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የድርቅ አደጋዎችን ለመቋቋም ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋል ። ባለስልጣኑ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ በተለይም በዋና ከተማይቱ በአዲስ አበባ እጅግ አስጊ የሆነ የምግብ ዕጥረትም ተከስቷል ።