1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድሬደዋና የትራፊክ ደህንነት ስልጠና

ሐሙስ፣ የካቲት 3 2003

አዉቶሞቢል የዛሬ 125ዓመት የተፈበረከባት ጀርመን የሚደርሰዉ ጉዳት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚከሰተዉ ጋር አይወዳደርም።

https://p.dw.com/p/Qzl7
...ለእግረና ቅድሚያ ይስጡ ...ምስል DW

ለዚህ ችግር ምናልባት እንደ ምክንያት ሊቀርብ የሚችለዉ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግን በአግባቡ ስለሚያከብሩ የሚለዉ ሊሆን ቢችልም የተሽካሪካሪዎቹ የዉስጥ ደህንነትም ሌላዉ ችግር እንደሆነ ይታወቃል። በድሬደዋ የሚደርሰዉን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ተማሪዎችን እያሰለጠኑ ነዉ። በተለያዩ 19 ትምህርት ቤቶች በተቋቋሙት የትራፊክ ደህንነት ክበባት አማካኝነት ተማሪዎች ራሳቸዉን ከአስከፊዉ አደጋ የሚከላከሉበትን መንገድ እንደሚያስተምሩም ተገልጿል። በከተማዊቱም ከመደበኛዎቹ ትራፊክ ፖሊሶች በተጓዳኝ በአሁኑ ሰዓት ከ200 በላይ የተማሪ ትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች እንዳሏት ለመረዳት ተችሏል። ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር ሁለት የትራፊክ ደህንነት ፖሊሶች ተማሪዎችን በሚያስተምሩበት ክፍል ተገኝቶ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ዮሐንስት ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ