1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዳንስ በናዚ ማጎርያ ጣብያ

ሐሙስ፣ መስከረም 13 2003

በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ግድም አይሁዳዉያን ላይ ከደረሰዉ ጭፍጨፋ የተረፉ አንድ የሰማንያ ዘጠኝ አመት አዛዉንትI will servive መከራን አልፊ እዚህ ደርሻለሁ ወደፊትም እቋቋሟለሁ ሲሉ በናዚ የማጎርያ ጣብያ ዳንኪራ መጨፈራቸዉ እዚህ በጀርመን ትልቅ ቁጣንን እና ዉይይትን ቀስቅሶ ሰንብቶአል።

https://p.dw.com/p/PLK2
አዶሌክ ኮንምስል youtube

I will servive እያለች Gaynor, Gloria ከያኒ በምታቀነቀንነት ሙዚቃ ከልጅ እና ከልጅ ልጆቻቸዉ ጋር አይሁዳዉያን በናዚ በግፍ በተገደሉበት ቦታ ላይ ሲደንሱ የሚያሳየዉን የቬዲዮ ፊልም በድረ-ገጽ ለአለም ይፋ ያደረጉት የሰማንያ ዘጠኝ አመቱ አይሁድ ጉዳይ በተለይ በዚህ በጀርመን ከፍተኛ ዉይይትን ቀስቅሶ ሰንብቶአል። በሁለተኛዉ አለም ጦርነት ግድም አዶሌክ ኮን ናዚዎች በአቋቋሙት የህዝብ ማጎርያ ማዕከል ዉስጥ ከብዙ ሽህ አይሁዳዉያን ጋር ታጉረዉ ታስረዉ አብዛኞቹ በጭፍጨፋ በግፍ ተገለዉ ሲያልቁ ከተረፉት በጣት ከሚቆጠሩ አይሁዳዉያን መካከል አዶሌክ አንዱ ነበሩ። የሰማንያ ዘጠኝ አመቱ አዶሌክ ኮን እንደ አዉሮጻዉያኑ አቆጣጠር1941 አ.ም ግድም በደቡባዊ ፖላንድ ናዚዎች አይሁዳዉያንን በሚያጉሩበት በአዉስሽቪትዝ ማጎርያ ጣብያ ታስረዉ ነበር። በደቡባዊ ፖላንድ አዉስሽቪትዝ በመባል የሚታወቀዉ የናዚዎች ማጎሮያ ጣብያ በተለያዩ ስፍራዎች ናዚዎች ለማጎርያ ጣብያነት ከአሰሩት ማዕከል መካከል እጅግ ትልቁ ሲሆን ጀርመናዉያኑ በተለይ በፖላንድ ለሚገኙ ፖለቲከኞች አይሁዳዉያን ማሰርያ አስበዉት የሰሩትም እንደነበር ይነገራል። የኪነ-ጥበብ ባለሞያዋ አዉስትራሊያዊትዋ የአዶሌክ ኮን ልጅ አባትዋን እና ልጆችዋን ይዛ ናዚ በግፍ ጭፍጨፋ ያደርግበት የማጎርያ ማዕከል ለመጎብኘት ወደ ፖላንድ ተጉዛ ነዉ፣ ናዚ አይሁዳዉያንን እያጎረ ይጨፈጭፍበት በነበረዉ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህይወታቸዉን ባጡበት ቦታ ላይ በመዘዋወር ከአባትዋ ከልጆቻቸዉ ጋር እንዲሁም እስዋ ጭምር I will servive የተሰኘዉን ሙዚቃ ከፍተዉ በመደነስ ፊልምን የተቀረጹት። እና ይህ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ የተፈጀበት ስቃዩን የበላበት ቦታ ይህን አይነት የዳንስ ፊልምን ቀድቶ ለአለም ህዝብ ይፋ ማድረግ ቅጥ ባጣ ሁኔታ ታሪክን መዘከር አይሆንም? በደቡባዊ ፖለን ባለዉ አዉስሽቪትስ የአይሁዳዉያን ማጎርያ ጣብያ ከሞት የተረፉት ደራሲ እና የፊልም ስራ አዋቂ ራልፍ ጊዎርዳኖ ይህን ዜና እንደሰማሁ ይላሉ ይህን ዜና ከሰማሁ ጀምሮ የምለዉ የምናገረዉ ጠፍቶኛል
‘’ዜናዉ ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ሳነበዉ በእዉነቱ በጣም ነዉ ያዘንኩት፣ የምለዉ ነገር ነዉ የጠፋኝ። በአንድ በኩል ይህ ሰዉ ይህን ሁሉ ስቃይ አልፎ ከልጅ ልጆቹ ጋር በመሆን እዚህ ቦታ ለመገኝት መብቃቱ በጣም የሚያስደስተዉ ነገር መሆኑ የማይካድ ነዉ። በሌላ በኩል በሚሊዮን የሚቆጠሩ እንደሱ ሳይተርፉ በጭፍጨፋ ያለቁበት ቦታ በመሆኑ ምነካዉ የሚለዉን ጥያቄ ያስነሳል’’

Holokaust Adolek Adam Kohn I will Survive
አዶሌክ ኮን ከልጅ ልጆቻቸዉ ጋርምስል AP

የዳንሱን ቪዲዮ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ በኤሌክትሮኒክሱ መገናኛ መረብ ኢንተርኔት በተለይም ዪቲዩብ ተብሎ በሚጠራዉ የተለያዪ የሙዚቃ ቪዲዮች ማሳያ መረብ ዉስጥ ብዙዎች አይተዉታል በጀርመን ይህ ጉዳይ ቁጣ በመቀስቀሱ እና ለዉዉይት በመዳረጉ ከዚህ ድረ-ገጽ ላይ መነሳቱም ተጠቅሶአል። በባቫርያ ግዛት በሙንሽን ከተማ የፊደራል ጀርመን ወታደሮች ዩንቨርስቲ ዉስጥ የታሪክ አዋቂ የሆኑት ሚሻኤል ዎልፍ ሶን ቪዲዮዉን ተመልክተዉ ለሰዉ ልጅ ህይወት መጥፋት ቅንጣት ያክል ስሜት የሌለዉ ጉዳይ ነዉ ብለዉታል። በተለይ ደግሞ የአዶሊክ ኮንን ልጅ አባትዋን እዚህ ቦታ ወስዳ ይህን ቪዲዮ መቅረጽዋ እራስዋን ታዋቂ ለማድረግ የፈጸመችዉ ነዉ ሲሉ ይፈርጅዋታል። በአዉስስቫይትዥ የናዚ ማጎርያ ጣብያ ታስረዉ የነበሩት ደራሲ ራልፍ ጊዮርዳኖ በበኩላቸዉ

“ይህንን ጉዳይ ስሰማ በእዉነቱ የምለዉ የምሰራዉ ነዉ የጥፋኝ፣ የአይሁድ ጭፍጨፋ ሲታወስ እጅግ የሚያሳዝን እና አንገት የሚያስደፋ ታሪክ ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ እዉነት ትክክል እና ጥሩ ነገር ነዉ የሰራዉ የሚለዉን ጥያቄ እራሴን መልሼ እንድጠይቅ ያስገድደኛል”
በሌላ በኩል በበርሊን ፍራይ ዪንቨርስቲ የታሪክ አዋቂ የሆኑት ዎልፍ ጋንግ ቪፐር ማን ይህ ቪዲዮ በይሁድ ላይ የደረሰዉን በደል በተለይም የግፉን ጭፍጨፋ ለመዘንጋት፣ አይሁዶች በእዚህ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ባለፈዉ ታሪክ ላይ ቢቀልዱ ተቀባይነት ያገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል። በአሁኑ ግዜ ከናዚ ግፍ ጭፍጨፋ የተረፉት ደራሲ ራልፍ ጊዮርዳኖ በበኩላቸዉ

“አሁንም ቢሆን ይህን ነገር በሁለት መንገድ መተርጎም ይቻላል። ለመናገርም ይከብደኛል። በእዉነቱ የተሰራዉን ነገር ለመፍረድ አስቸጋሪ ነዉ። መሄጃ መጨበጫ ነዉ የሚያሳጣዉ። እንደኔዉ እድለኛ ሆኖ የአይሁዳዉያን ላይ የተደረገዉን የግፍ ጭፍጨፋ የተረፈ ግለሰብ፣ ይህንን ድርጊት ፈጽመሃል እና ትክክል አይደለህም ብዪ ልኮንነዉም አልሻም። ግኔ እኔ ግን በበኩሌ በእሱ ቦታ ብሆን ይህን ድርጊት አልፈጽም ነበር። በአጠቃላይ ይህንን የግፍ ድርጊት አልፎ ዛሪ በህይወት መኖር እራሱ አንድ ትልቅ እድል ነዉ! እኔም እራሴ ብሆን ብሆን! የተረፍነዉም በመርፊ ቀዳዳ የመሽሎክ ያህል እድል አጋጥሞን ነዉ። ስለዚህም ይህንን አስከፊ የስቃይ ግዜ ማለፉ በራሱ ደስታ ትልቅ እድል መሆኑ መረሳት የለበትም”

ይህን ቪዲዮ ያዩ በጀርመን ታዋቂ የሆኑ አይሁዳዉያን ጉዳዩን ለሰዉ ልጅ ምንም ስሜት የሌለዉ ጉዳይ ሲሉ መግለጻቸዉ ተዘግቦአል። በበርሊን የይሁዳዉን ማዕከል ቢሮ ምክትል ተጠሪ የነበሩት ሚሻኤል ፍሪድማንም በበኩላቸዉ በቪዲዮዉ ላይ የቀረበዉን ነቀፊታ በመደገፍ አዉስሽፊትስ የናዚዎች የማጎርያ ጣብያ የነበረዉ የመደነሻ ቦታ ሳይሆን የሃዘን መግለጫ ሙታንን ማስታወሻ ቦታ መሆኑን አመልክተዉ፣ ይህ የዳንስ ቪዲዮ ለሙታኑ ክብር ያልተሰጠ መሆኑን ጠቋሚ ነዉም ብለዉታል።
የሰማንያ ዘጠኝ አመቱ አዶሌክኮን የድል ምልክት ያለበት ቲሸርት ለብሰዉ ከልጅ ልጆቻቸዉ ጋር ሲደንሱ በሚታዩበት ቪዲዮ ላይ ‘ይህ አንድ ታሪካዊ ክስተት ነዉ’ ሲሉ መናገራቸዉም ይደመጣል። በበርሊን ቢልድ በተሰኘዉ ጋዜጣ ላይ አስተያየታቸዉን ያሰፈሩት ጀርመናዊዉ ደራሲ ራልፍ ዚግልማን በደቡባዊ ፖላንድ የሚገኘዉ አዉስሽቪትዝ የናዚ የማጎርያ ጣብያ በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ እጅግ አሰቃቂ ታሪክ የተፈጸመበት ቢሆንም ዘላለም በሃዘን ማሰቡ ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ አይሁዳዉያንም ሆኑ ሌሎች ግፍ የተፈጸመባቸዉ ወገኖች ምንም እንኳ አስከፊ ነገር ቢደርስባቸዉም የደስታ ህይወት በልጆቻቸዉ በልጅ ልጆቻቸዉ በራሳቸዉም ላይ እንዳለተለየ ማሳየት ይኖርባቸዋል ሲሉ አስፍረዋል። ይህም ይላሉ ጸሃፊዉ ህይወት ሞትን ድል ማድረጉን ያንጸባርቃል ሲሉ ጽፈዋል። I will survive በተሰኘዉ Gaynor, Gloria ሙዚቃ ከልጅ ልጆቻቸዉ ጋር በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዳዉያን በግፍ በተገደሉበት ቦታ ላይ የደነሱት 89 አመቱ Adolek Kohn በሰሩት ስራቸዉ አንዳንድ ደጋፊዎችን ያገኙ እንጂ በአብዛኛዉ ከፍተኛ ነቀፊታና ክብር የሌለዉ ስራን መስራታቸዉ ተመስክሮባቸዋል። ናዚ እናታቸዉን ዘመዶቻቸዉን የገደለባቸዉ Adolek Kohn በየአመቱ ፖላንድ አዉስሽቪትስ እየመጡ የሚዘክሩት ከአዉሮጻዉያኑ 1949 ጀምሮ ከናዚ ብትር ከተረፉት ባለቤታቸዉ ከዝያም ከፈሩዋቸዉ ሁለት ሴት ልጆቻቸዉና ልጅ ልጆቻቸዉ ጋር በአዉስትራልያ ሜልበርን ይኖራሉ።

አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ